Tesfaye Gabiso

"እንደተቀበልኩት ምህረት እንደቸርነትህ ብዛት እንዳገለግልህ እርዳኝ ጌታ ሆይ ስጠኝ የመንፈስን እሳት"-በዚህ ብሎግ እውነተኛው የጌታ ኢየሱስ ባሪያ ተስፋዬ ጋቢሶ ይታወስ ዘንድ ወሰንን።This blog has been dedicated to Tesfaye Gabiso,the faithful servant of The Lord.

Saturday, 18 May 2013

ሠላም ለኩሉ ክብር ለስሙ

ሠላም ለኩሉ ወዲህ ለመጡ በሙሉ - በእግዚአብሔር አምላክ በምህረቱም ብዛት በፍቅሩም ጉልበት በሕይወት ከሚኖር::

ክብር ለዘለዓለም ክብር ለስሙ ይሁን::
Amen.

Tuesday, 14 May 2013

ሊረዳኝ

በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ብሆን ሊረዳኝ ሊያወጣኝ ይችላል:: ሊረዳኝ ይችላል::
አዎና ሊረዳኝ ይችላል::

የልቤን አበባ የልቤን ኣትክልት

Image source: Wikipedia

የልቤን አበባ የልቤን ኣትክልት

አይታ...ችሁ  እለፉት

እንዳትነካኩት::

***

-ያሁኑን ኣላውቅም ከጥንት የአስቴር መዝሙሮች የተገኘ እንደሆነ አልደብቅም::

እወድሃለሁ

እወድሃለሁ ጌታ እወድሃለሁ እየሱስ 

Saturday, 11 May 2013

ንጉሥ ሆይ የሚል መዝሙር


Pls kindly  forgive audiovisual/technical  quality. For a better listening experience , pls use a Headphone-as this video is a casual record just for your ears only, really.

***
This song is about a story of people who sometimes ago went to see the King of the dominion for they were terribly hungry and thirsty.

They marched and approached  the palace in search of food and drink -and cried out loudly just for food and water.

Suddenly the king of the nation appeared through the window of the palace, at which very moment the people completely forgot their cry and found themselves singing this very song.

Hoy Negus Hoy::

***
Recorded by a friend using a good old phone devise during a Kensington Temple (London and the World for CHRIST) London City Church- The  Encounter Epic Journey ,Annan Court,East Sussex . (Yea, it was 'recorded' during the break )

October 2012
_________________________

ሆይ ንጉሥ  ሆይ
ንጉሥ  ሆይ
ሆይ ንጉሥ  ሆይ።


እንጀራ እጥተን ተርበን
ውሃንም ጠምቶን ተቃጥለን
እያለን
ጌታ አረካኸን።

ሆይ ንጉሥ  ሆይ ...
________________________________________

እስቲ እንወያይ አንድ ቤተሰብ አይደለንም አንዴ ምነው? ፡ሕዝቡ በንጉ  መታየት ብቻ በደስታ ሰክሮ ወደቤቱ የተመለሰበት  ምክንያት  ምን ይመስልዎታል?

Friday, 10 May 2013

የደምህ ምንጭ

በጎልጎታ የፈሰሰው የደምህ ምንጭ ነፍሴን ያንጻው

Wednesday, 1 May 2013

ሕይወቴ ለሕይወት ልዕልና


በጉልበቱ  እና በደረቱ  በግንባሩ በሕይወት ፊት ተደፍቶ - ከእንግዲህ ሲል ተማጸነ -
ከእንግዲህ ሕይወቴ ለክቡር ሕይወት ደስታ ይሁን ብሎ እያለ በማለት ተማጽኖውን በዕንባ መስዋዕት አሳረገ።

Saturday, 27 April 2013

አንተ ታማኝ አንተ ታላቅ::


ጌታ ሆይ አንተ ታማኝ አንተ ታላቅ ከሁሉ በላይ ነህ
አንተ ብቻ አለህ::

Thursday, 25 April 2013

Wednesday, 17 April 2013

Sunday, 14 April 2013

የኔ

ኢየሱስ ጌታዬ እና አምላኬ::

Saturday, 13 April 2013

Monday, 1 April 2013

ሬማ ማንቼ AIR Ways


****

ሬማ ማንቼ AIR Ways: Going Great Miles To Praise The LORD.

 ።።።

Cabin Crew:
(ፈጠን ቀጠን ቀልጠፍ ባለ የሆስተስ ድምጽ ምሳሌ) :

ክቡራን እና ክቡራት መንገደኞቻችን በሬማ ማንቼ  Air Ways ስም እንኳን ደህና መጣቹ በማለት የማስተናግዳች እታለም ግርማቸው  ነኝ፡፡

በዛሬው ዕለት ይዘውን የሚበሩት  ካፕቴይን አያሌው ምህረትቸርነቱ ሲሆኑ ረዳት አብራሪያቸው  ሻምበል ወንድማችን መልካምሰው ናቸው፡፡

ፕሌ ኑ ቴክ ኦፍ ሊያደርግ ስለሆነ ክቡራን እና ክቡራት  መንገደኞቻችን ቀበቷችሁን እንድታስሩ በጥብቅ  ትህትና እንጠይቃለን፡፡

***

ካፕቴይን አያሌው :
(በጎርናና ወፍራም ጀንተል ያለ የካፕቴይን ድምጽ ምሳሌ)

ዚስ ኢዝ ካፕቴይን አያሌው ምህረትቸርነቱ ስፒኪንግ ፍሮም ፍላይት ሩም .... እ...ኣው - ይህ ካፕቴይን አያሌው ነው የሚናገረው ::ካፕቴይን  አያሌው  በድጋሚ በሬማ ማንቼ Air Ways፣በረዳት አብራሪያቸው በሻምበል ወንድማችን መልካም ሰው፣
እንዲሁም ደግሞ  
በ Cabin Crew የስራ ባልደረቦቻችን ስም በድጋሚ እንኳን አውሮፒላናችን ላይ ወጣቹ ወይም ተሳፈራቹ በማለት ሰላምታዬን አቀርባለሁ፡፡

በአሁኑ ሰዓት ከባሕር ወለል በላይ ብዙ ሺህ ጫማ ከፍ ብለን በመብረር ላይ እንገኛለን::

የአየሩ ሁኔታ መልካም እና ብርሃናማ ነው:: በጥቂቱ ከፊል ደመናማ ሲሆን ጥቂት ቆይቶ ጥርት ሊል ይችላል፡፡ሰማይ ብቻ ነው የሚያውቀው፡፡

***

Cabin Crew:  

ከበረራ መስተንግዶ ክፍል በድጋሚ እታለም ግርማቸው ነኝ::ክቡራን እና ክቡራት  ቀበቷችሁን አሁን መፍታት ትችላላቹ፡፡ ጥቂት እልፍ ብለን  ሻይ ቡና እንዲሁም የሬማ ማንቼ Air Ways  ስናክ እና ቀለል ያሉ የሚቀመሱ ነገሮችን ያቀርብላችኋል፡፡


በዚሁ ሂደት ሬማ ማንቼ Air Ways ለዕለቱ  የመረጠላችሁን ሙዚቃ ይጋብዛችኋል፡፡


***

ካፕቴይን  አያሌው:

ክቡራን እና ክቡራት ከበረራ ክፍል በድጋሚ ካፕቴይን  አያሌው ይናገራል፡፡በአሁኑ  ሰዓት አየሩ ጥሩ ሲሆን ወደ ማረፊያችን እየተቃረብን ነው::

ፊታችሁን  ወደግራ  እንዲሁም  ወደቀኝ ዘወር በማድረግ ልዩ ልዩ
የአየር ጸባይ ሁኔታዎችን እና የመልክአ ምድር አቀማመጦችን ማየት ትችላላቹ፡፡

በአሁኑ ሰዓት በአመፃ ኮረብቶች በመገረም ፣ የትዕቢትን ኩሬ እና የቅጥፈትን ጅረት በስተግራ በመተው ፣የጨለማውን ዓለም ከበስተኋላችን በከባድ ርቀት በመለየት ፣የአመፃን ባሕር ተሻግረን ፣ የክፋትን ውቅያኖስ አቋርጠን   አደገኛ ተራሮችን በስተግራ በመተው ፣ የጥፋትን ሸለቆ  በደመና የሕይወት ክንፎች ተሻግረናል::

********
Cabin Crew:

ክቡራን እና ክቡራት : ወደ His Mercy Endures Forever International Airport  ስለተቃረብን እና ወደ እረፍት Run Way  ዲሰንት እያደርግን ስለሆነ ወገባችሁን በእውነት ቀበቶ እንድታጠብቁ ፣ በመዝናናት እንዝላልነት የፌዝ ጎዳና ላይ ያላቹ አርፋቹ እንድትቀመጡ እያሳሰብን ፣ሬማ ማንቼ Airways ከእኛ ጋር ለመጓዝ በመምረጣቹ  ምስጋናውን እያቀረበ መልካም ቀን ይመኝላችኋል፡፡
___________________________________

*** *** ***
እኛም በክርስቶስ ፍጹም የሚሆን ሰውን ሁሉ እናቀርብ ዘንድ
ሰውን ሁሉ እየገሠጽን ሰውንም ሁሉ በጥበብ ሁሉ እያስተማርን
የምንሰብከው እርሱ ነው።
 -ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1:28

*** *** ***
___________________________________



ከዚህ በላይ ያነበቡት ስነ/ኪነ ጥበባ መንፈሳዊ መልክት 
ለኛ ለሁላችን በሬማ ማንቸስተር ጌታን ኢየሱስን በንጹህና በቅን ልብ
በበጎም ህሊና ሁሉ ሊያመልኩ በሚወዱ ወንድሞች  ከቀረቡት ፕሮግራሞች አንዱ ነው

የ2013 የትንሳኤውን መታሰቢያ በዓል ምክንያት በማደረግ::

በዚሁ ዕለት ግሩምድንቅ የሆኑ የሕጻናት መዝሙሮች፣ጭውውቶች
ግጥሞች   መልእክቶች እና ሌሎችም ዝግጅቶች ቀርበዋል::

ክብር ለስሙ::

ጌታ ሆይ

ጌታ ሆይ ክብር ለዘለዓም ለስምህ ይሁን::