»

እንደተቀበልኩት ምህረት እንደቸርነትህ ብዛት እንዳገለግልህ እርዳኝ ጌታ ሆይ ስጠኝ የመንፈስን እሳት"-በዚህ ዌብሎግ እውነተኛው የጌታ ኢየሱስ ባሪያ ተስፋዬ ጋቢሶ ይታወስ ዘንድ ወሰንን።This weblog has been dedicated to Tesfaye Gabiso,the faithful servant of The Lord.

Saturday, 16 October 2010

የተጠማ ብርጭቆውን አንስቶ ውሃውን ግጥም።እፎይ አምላኬ አረፍኩኝ ከጥሜ ብሎ እህም።ያልተጠማ በብርጭቆው ዙሪያ ሽክርክሪት  መድገም።

Friday, 15 October 2010

እግዚአብሔርን ከልቡ የሚፈራ ልጁን ኢየሱስን ከልቡ ይወዳል።

Thursday, 14 October 2010

ትዕቢት እና ቅናት ያንድ ሳንቲም ሁለት ባህርያት።ምሳሌ ሰይጣንን መመልከት።መፍትሄ አቤቱ ትሁት ንጹህ አድርገኝ የሚል ጸሎት።

Monday, 11 October 2010

በመጀመሪያም ሲል ከመጀመሪያ በፊት ጀምሮ ሊሆን ይችላል።

Sunday, 10 October 2010

አንዳንዶች እስከ አሁኗ ደቂቃ ድረስ ውበት ላይ አፍጥጠዋል(እንቅልፍ ይዟቸው ሄዶም ሊሆን ይችላል)።ሌሎች የውበትን ደራሲ ፍለጋ እልፍ ብለዋል።
በማየት ካለማየት ባለማየት ማየት ሳያሳይ አይቀርም።

Saturday, 9 October 2010

"ነገ "ሲል "ትላንት" ማለቱ እንዳይሆን።

Friday, 8 October 2010

ወንድሜ መልካም ስለሆነለት ደስ አለኝ።

Thursday, 7 October 2010

አበበ የህይወት ትርጉም ሞት ነው አለ። አይደለም-የህይወት ትርጉም ከሞት ባሻገር የዘላለም ህይወት ነው እንጅ ሲል ከበደ የእምነት ቃሉን ሰጠ።