Pages

አለምልመው

አባት ሆይ ይህን ብላቴና ባርከው አለምልመው ቀድሰው::


ጌታ ሆይ ስለዚህ ወንድማችን ኤልያስ እናመሰግንሃለን:: በኢንተርኔት ፣በከተማ በጎዳናው ፣በቤተክርስቲያን ሁሉ ያገለግላል::

ጌታ ሆይ ይህ ብላቴና ቅኔ ሲቀኝ፣ምሳሌ ሲነግረን፣መዝሙርም ሲዘምር ፤ለስምህም ያለውን ፍቅር፣ለቤተመቅደስህም ያለውን ቅናት ፣ለሕዝቦች ህም ያለውን በጎ ልቡና እናያለን::

ሰውን ሳያይ ከሰውም ምንም ሳይጠብቅ እንዘምር እንቀኝ እንመስክር እያለ እኛንም ያነቃቃናል::

ምድርን ቸል በማለት ሰማይን ለማክበር ይወዳል::

አቤቱ ጌታ ሆይ ይህን ወጣት ሰው ውድ የሆኑትን ቤተሰቦቹንም ሁሉ በፈቃድህ ፍጥነት በምህረትህ ብዛት በፍቅርህም ጉልበት  በሰማይ እና በምድር በረከት በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ባርከው::

ስምህ ለዘለዓለም ብሩክ ይሁን ጌታ አምላክ ሆይ::

You Klick Amen.