»

እንደተቀበልኩት ምህረት እንደቸርነትህ ብዛት እንዳገለግልህ እርዳኝ ጌታ ሆይ ስጠኝ የመንፈስን እሳት"-በዚህ ዌብሎግ እውነተኛው የጌታ ኢየሱስ ባሪያ ተስፋዬ ጋቢሶ ይታወስ ዘንድ ወሰንን።This weblog has been dedicated to Tesfaye Gabiso,the faithful servant of The Lord.

ቡራኬ ለሕዝቦች ሁሉ

ቡራኬ ክፍል
ለሕዝቦች ሁሉ::

(ብላቴናው ዘመድዎ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 15 ቁጥር 5 መሠረት ከዚህ በታች እርስዎ የሚቀበሉትን በጎ የበረከት ቃላት በክርስቶስ ኢየሱስ ስም ተናገርኩ - “...ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና ...” የሚለውን  የጌታን ቃል  ዘመድዎ ስረዳው : -  -እኔ ከሆናችሁ ግን ፣የ-እኔ ከሆናችሁ ግን
ለ-እኔ ከሆናችሁ ግን ፣ከ-እኔ ከሆናችሁ ግን ሁሉንም ነገር ማድረግ ትችላላችሁ:: ክብር ለስሙ ይሁን :: ጸሐፊው እጅጉን አሜን ይላል ::


ቡራኬ ››


›› ለእግዚአብሔር አምላክ ልጁምኢየሱስ ክርስቶስ  አጋዣችንና ወደ እውነት ሁሉ መሪያችን ለሆነው ለጌታ መንፈስ ቅዱስም ክብር ይሁን::

ሕዝቦች ሁሉ ‹‹አሜን››ይላሉ::


›› የተጣመመች ነፍስ ያለችን እኛ ሁላችን ነፍሳችን በጌታ በኢየሱስ ስም ትቃናልን::

ሕዝቦች ሁሉ ‹‹አሜን››ይላሉ::

›› አንድ እግራችን ቤተክርስቶስ ውስጥ አንድ እግራችን በድቅዱ ጨለማ(በዓለም ውስጥ) የተንሸራተተብን ሁላችን በጌታ ስም እግራችን ወደ ሰላም ሕይወት ጤና ቤት ይመለስልን::

ሕዝቦች ሁሉ ‹‹አሜን››ይላሉ::


›› እናንት በዓለም ላይ በመዝናናት ላይ ያላችሁ እየመሰላችሁ በመባለግ  ብክነት ጉዳት ላይ ያላችሁ በሙሉ ባላችሁበት እንድትቆሙ እናዛለን::ከድቅድቁ ጨለማ ኑሯችሁ  - ቅሌን ጨርቄን(ገንዘቤን ንብረቴን...አክስቴን አጎቴን ...) ሳትሉ ወደ ሚደነቀው ብርሃናችሁ  ወደ ክርስቶስ ኢየሱሳችሁ  ዛሬ በመዳን ቀን  ዘወር እንድትሉ እንመክራለን::


[ሰዎች ሁሉ ወደ ክርስቶስ ዘወር ይላሉ:: 

(የቤት ልጆችም ሁሉ ‹‹አሜን››ይላሉ (ወንጌል ይሰብካሉ ፣ይመሰክራሉ፣ወንጌል ሰባኪዎችንም 
በጸሎታቻው  ያግዛሉ ፣ ይደግፋሉ  
ሠራተኞችም ደግሞ የቅሌስ  የጨርቄስ ጉዳይ 
ለእኔስ የእኔስ እያሉ እንዳይተክዙ 
ከቅላቸው እና ከጨርቃቸው ያካፍላሉ ::]


›› ሥራ አጥተን የምንንከራተት እኛ ሁላችን ሥራ እናገኝ ዘንድ በጌታ ስም ይሁን::

ሕዝቦች ሁሉ ‹‹አሜን›› ይላሉ::

[ይህ ቡራኬ ስራ እናገኝ ዘንድ
(በእናት አገር ቢሆን በዳያስፖራ ብንኖር
ፍላጎተኞች እንድንሆን ያዛል:: 
ወይ ወደ ስራ ፍለጋ ወይ ወደ ስራ ፈጠራ
እንድንሰማራ አክሎ ያስረግጣል::]


›› የጌታ እግዚአብሔርንም ስራ አብዝተን በመስራት ላይ ያለን እኛ ሁላችን አጥርተን ደግሞ እንድንሰራ የሚደነቀው ብርሃን
በአገልግሎታችን በሕይወታችን እጅጉን ይብራልን::

ሕዝቦች ሁሉ ‹‹አሜን››ይላሉ::


›› ቀን በሀሳብ ትካዜ፣ምሽት በፍራት ድንጋጤ፣በመንፈቀ ሌሊትም በቅዠት ኩነኔ የምንረበሽ ሁላችን የክርስቶስ ኢየሱስ ዘላለማዊ ሠላም እንደወንዝ በልባችን ይፍሰስ ፤ ምንጩንም እልባችን ያድርግ::

ሕዝቦች ሁሉ ‹‹አሜን››ይላሉ::

(እባክዎ  “ሠላምህ እንደወንዝ በልባችን  
ፈሰሰ ምንጩን እልባችን አደረገ...” 
የሚለውን መዝሙር ይጋበዙ::)


›› ሕዝቦች ሁሉ ክብር ለስሙ ለጸሐዩ ንጉስ  ለክርስቶስ ኢየሱስ የአምላክ ልጅ  ይሁን ይላሉ::

ሕዝቦች ሁሉ አሜን ይላሉ::