»

እንደተቀበልኩት ምህረት እንደቸርነትህ ብዛት እንዳገለግልህ እርዳኝ ጌታ ሆይ ስጠኝ የመንፈስን እሳት"-በዚህ ዌብሎግ እውነተኛው የጌታ ኢየሱስ ባሪያ ተስፋዬ ጋቢሶ ይታወስ ዘንድ ወሰንን።This weblog has been dedicated to Tesfaye Gabiso,the faithful servant of The Lord.

በረከተ -ኢትዮጵያ





በረከተ-ኢትዮጵያ። Blessings Ethiopia.


እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያን ይባርክ::አሜን።

May The Good Lord bless Ethiopia. Amen.


እግዚአብሔር አምላክ የሃይማኖት መሪዎችን ይቅር ይበል ይባርክም::አሜን።

ሰላም እና ጽድቅን ፤እውነትን እና ፍቅርን እንዲሰብኩ ሳይሆን እንዲኖሩ፣እንዲያሳዩ፣እንዲሰሩም።አሜን።
May The Good Lord forgive and bless the religious leaders. Amen.


So that they will not be only preachers of Righteousness, Truth and Love ,but also doers and exemplary leaders. Amen.




እግዚአብሔር አምላክ የመንግስት ባለስልጣናትን ይቅር ይበል ይባርክም።አሜን።

በስልጣን እንዳይባልጉ ፍርድንም እንዳያዛቡ።አሜን።
May The Good Lord forgive and bless the government officials. Amen.
So that they will not abuse authority and practice injustice. Amen.



እግዚአብሔር አምላክ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ይቅር ይበል ይባርክም።አሜን።

በሰላም ጽኑ ተቃዋሚዎች ይሆኑ ዘንድ።አሜን።
May The Good Lord forgive and bless the Opposition parties. Amen.
So that they firmly and peacefully oppose. Amen.



እግዚአብሔር አምላክ ገዥውን ፓርቲ ይቅር ይበል ይባርክም።አሜን።

በተሰጠው ጊዜ ፍርድን እና ፍትኅን እንዳያዛባ።ሕዝብንም እንዳያስከፋ።ያስከፋም እንደሆን ይቅርታን እንዲጠይቅ እጅግም ፈጥኖ እንዲታረም።አሜን።
May The Good Lord forgive and bless the ruling party. Amen.
So that in the time it is given it will not do injustice ,will not dismay the people, and if it did ,it apologizes and corrects itself so in time. Amen.




እግዚአብሔር አምላክ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ባለስልጣናትን ይቅር ይበል ይባርክም።አሜን።

ለፍትህ ለልማት እና ለብልጽግና የዋለን ስጦታ እንዳያባክኑ።አሜን።
May The Good Lord forgive and bless the NGO officials። Amen.
So that they will not abuse charity. Amen.



እግዚአብሔር አምላክ ነጋዴዎችን እና ባለሀብቶችን ይቅር ይበል ይባርክም።ገንዘብ አምላኪ ሆነው ሕዝቡን እንዳያስመርሩ፣በንዋይ ፍቅርም ታውረው ገደል እንዳይገቡ።አሜን።

May The Good Lord forgive and bless merchants and investors. Amen.
So that they will not be worshipers of money who quickly end up in the pit. Amen.



እግዚአብሔር አምላክ ወዛደሮችን፣ወታደሮችን፣ገበሬዎችን፣ተማሪዎችን፣አስተማሪዎችን፣ተመራማሪዎችን፣ሠራተኞችንሁሉ ይባርክ ይቅርም ይበል።አሜን።

May The Good Lord forgive and bless labourers ,soldiers ,farmers ,students, teachers, researchers and all workers. Amen.



እግዚአብሔር አምላክ ከኢትዮጵያ እና ከኤርትራ ሕዝቦች ላይ ቀንበርን ይስበር። አሜን።

የድህነትን ፣የኢኮኖሚን ፣ የሃይማኖትን፣የፖለቲካን ፣ የባህልን፣ የማሕበራዊ እስራቶችን እና ጭቆናዎችን ሁሉ ይስበር።በጌታችን እና በመድሃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በሰማይ እና በምድር እንክትክቱ ይውጣ።አሜን።
May The Good Lord break the yoke from the peoples of Ethiopia and Eritrea. Amen.
We command ,in the Name of The Lord Jesus Christ The Son of God ,The bondages of poverty ,economy , religion ,politics and cultural entanglements to be broken in heaven and on hearth. Amen.




እግዚአብሔር አምላክ በምድሪቱ ላይ የሚሰለጥነውን እርግማን ይስበር።አሜን።

May The Good Lord break any curse prevailing in the land. Amen.




እግዚአብሔር አምላክ አባቶቻችን በጥንት እና በቅርብ ዘመን የሰሩትን እኛ የምናውቀውን እኛም የማናውቀውን ኃጢያት እና በደል ሁሉ ይቅር ይበል ።አሜን።

May The Good Lord forgive the terrible sins of our ancestors which we know; and which we do not know. Amen.




እግዚአብሔር አምላክ የኤርትራን እና የኢትዮጵያን ልጆች ይቅር ይበል ይባርክም።አሜን።

May The Good Lord forgive and bless the children of Ethiopia and Eritrea. Amen.





እግዚአብሔር አምላክ በጽኑ ክንዱ በበረታችም ኃይሉ በሀገረ-ኢትዮጵያ በሀገረ-ኤርትራም ይክበር።አሜን።

May The Good Lord by His Stretched Arms and Mighty Power be glorified in Ethiopia and Eritrea. Amen.




እግዚአብሔር አምላክ በሀገራችን ኢትዮጵያ ያሉ ብሔር ብሔረሰቦች ሁሉ በእኩልነት እና በነጻነት የሚቻቻሉበትን መለኮታዊ ጸጋ ፤ እንዲሁም ተከባብረው በአንድነት የጋራ ጠላታቸው የሆነውን ድህነትን፣ጨለማን፣ድንቁርናን ፣ግትርነትን፣ክፋትን ፣የስህተት አሰራርን ሁሉ የሚዋጉበትን ጸጋ እና የመንፈስ አንድነትን ይስጣቸው።አሜን።

May the Good Lord grant the Divine Grace which enables all nations and nationalities in Ethiopia and Eritrea to love and respect one other ;the Grace and the Unity of the spirit which transforms them to fight their common enemy which is poverty, darkness, ignorance ,arrogance ,evil and all other catastrophic and erroneous belief systems. Amen.



የእግዚአብሔር አምላክ ቅዱስ መንፈስ በኢትዮጵያ ያለመከልከል በኃይል ይሰልጥን።አሜን።

May The Spirit of The Lord prevail in Ethiopia without being blocked by unbelief. Amen.




እግዚአብሔር አምላክ የኢትዮጵያን እና የኤርትራን ሰው ሁሉ ይባርክ።አሜን።

May The Good Lord bless the peoples of Ethiopia and Eritrea. Amen.




እግዚአብሔር አምላክ በሀገረ-ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሰላም፣ብልጽግና፣ምህረት፣ጸጋ፣ፍቅር፣መቻቻል፣ደስታ ሁሉ እንዲበረክት ያድርግ።አሜን።

May The Good Lord cause Peace, Prosperity, Mercy, Grace, Love, Tolerance and Happiness in Ethiopia and Eritrea. Amen.




እግዚአብሔር አምላክ የሚወዱንን እና የምንወዳቸውን ጎረቤቶቻችንን የጅቡቲን ህዝብ፣የሱማሌን ህዝብ፣የኬንያን ህዝብ፤የሱዳንን ህዝብ ፤የኤርትራን ህዝቦች ሁሉ ይቅር ይበል ይባርክም።አሜን።

May The Good Lord forgive and bless our neighbours and friends ,the great nations of Djibouti ,Somali ,Kenya ,Sudan and Eritrea. Amen.


እግዚአብሔር አምላክ በመላው ዓለም ወዳጆቻችን የሆኑ ፤በችግራችንም ሰዓት ያስጠጉንን እና የረዱንን ሕዝቦችን እና መንግስታትን ሁሉ ይባርክ።

May The Good Lord bless all Nations and Sovereignties in the world who gave us shelter and support in our times of need.


በአብርሃም በይሰሃቅ በያዕቆብ ህያው አምላክ በእግዚአብሔር ስም እነዚህን በረከቶች ተናገርኩ ፣ይህንም ጸሎት ጸለይኩኝ።አሜን።

In The Name of The Lord The Living God of Abraham, Isaac and Jacob, I prayed and uttered these blessings. Amen.




የእግዚአብሔር አምላክ ስም ከዘለዓለም እስከዘለዓለም በሰማይና በምድር ሁሉ የተባረከ ይሁን።

አሜን።
Blessed be The Name of The Lord Throughout The Universe in All Eternity.
Amen.


የእግዚአብሔር አምላክ ስም በዘመናት እና በዓለማት ሁሉ የተባረከ፣ የተቀደሰ፣የተከበረም ይሁን።



አሜን።



***



ማስታወሻ።



ውድ ያገሬ ሰው ሆይ ፤

ሠላም ላንተ ይሁንልህ።


እኔ ዘመድህ ለሀገሬ ኢትዮጵያ ያለኝ ፍቅር ፈንቅሎኝ ለጎረቤቶቼም ከበሬታ ኖሮኝ የልቤን እና የውስጤን ምኞት፣ጸሎት ፣የበጎ ኀሊና ምስክርነት ሁሉ ኢንተርኔት በሚሉት ወንበዴ ሰደድኩልህ።



“ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው” የሚለው የጌታ ቃል አንቀሳቅሶኝ ነው።ደሞ በረከት አድርጉ ፣አስታራቂ ሁኑ …ብርሃን ናችሁ …ብሎ ታላቁ ህያው መምህር ተናግሯል-ክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ።



ታዲያስ- ምነው ያገሬ ሰው ሆይ?



በረከት ነህ ማለትን አንተ እንዴት እንድታየው አላውቅልህም። አንድ ወቅት ላይ ከትላንት በስቲያ እኔ ራሴ ከራሴ ውጭ የማላስብ ምስኪን ሰው ብቻ የሆንኩኝ ተላላ ነበርኩኝ።እና ታዲያ አሁን ምን አገኘህ ትለኝ ይሆናል፤ ክርስቶስ ኢየሱስን አገኘሁት።እውነቱን እነግርሃለሁ ያገሬ ሰው ሆይ ክርስቶስ ዓለም ሳይፈጠር በፊት ያገኘኝን ማግኘት ነው እኔ ዛሬ ያገኘሁት።እርሱ አስቀድሞ ሳልፈጠር ፈጥሮ የወደደኝን መውደድ አውቅ ዘንድ ተፈጠርኩ እነሆም ተገኝሁ።ያገሬ ሰው ሆይ ከእናት ከአባትህ ተወልደህ የሆነልህን ራስህን ቸል ብለህ በክርስቶስ ያለውን እራስህን ብትፈልግ እና ብታገኝ ይበልጥብሃል። አያሳፍርህም ይገኝልሃል። ክርስቶስን እየተረዳሁ ከመጣሁ ጀምሮ በረከት ማለት ሰላም ወዳድነት ፣ታራቂነት፣አስታራቂነት፣የዋህነት፣በጎነት፣ሀገር ወዳድነት ፣ይቅርታ ጠያቂነት ፣ይቅር ባይነት…ሁሉ እንደሆነ ገባኝ እንጂ ።



 ብላቴናው ዘመድህ በምችላቸው ቋንቋዎች ተጠቅሜ ጻፍኩልህ።አልዋሽህም። አንተ ደግሞ በአደሬ ቢሆን በኦሮምኛ ቢሆን፣በትግርኛ ቢሆን፣በአፋርኛ ቢሆን ፤በአገው ቢሆን ፤በጉራጊኛ ቢሆን፤በወላይትኛ ቢሆን፤በሲዳምኛ ቢሆን፤ በሀድየኛ ቢሆን፤ በጌዲኦ ቢሆን፤በጋሞ ቢሆን ፤በከፊቾ ቢሆን፤በከምባትኛ ቢሆን እረ ውድ እና ብርቅዬ በሆኑት የወገንህ ቋንቋዎች ሁሉ ተጠቅመህ ይህን የበረከት ቃል በቻልከው ቋንቋ ሁሉ ተርጉመህ፤ በቦስጣ ቢሆን፤በኢሜል ቢሆን፤ በወንበዴው ቢሆን ፤በሰው ቢሆን ፣በፕሪንት አውት ቢሆን፣ በፋክስ ቢሆን አሰራጨው፤ይሂድም ፣ይናኝም ፣ወደሰው መንፈስ ውስጥም ይህ ሰላም፣ተስፋ፣እርቅ፣ፈውስ…ይስረጽ።



የሕዝባችንም አንደበት ሰላምን እና ፍቅርን ተንፋሽ፣ምላሱም ምህረትን እና በጎነትን ተኳሽ ፣ልቡናውም ተስፋ አፍሳሽ ፣ፈቃዱም በጎ ቀያሽ ይሁንለት።



ለሰው የማይቻል ለእግዚአብሔር እንደሚቻል ተጽፎልሃል።ጌታ አምላካችን ደግሞ በደልን ይቅር የሚል አመጻን የሚያሳልፍ አምላክ ነው።



ምነው ያገሬ ሰው ሆይ?



እናት ሀገርህ ከዓለም በሩጫ እና በድህነት ብቻ አንደኛ ሆና ስትሮጥ አያሳዝንህም?

ዓለም ሁሉ ነቅሎ በተሌቢዥን ሲያያት?


በከተማው በመንደሩ የአንተ እናት ብቻ ነጠላ የሌላት ብቸኛዋ ሴት ብትሆን ሆድህን አያምህም ፤ልብህን አይጎዳህም ፣ምነው ያገሬ ሰው ሆይ?



ይህን ዓለም የሚያህል ጉዳት ተሸክመህ እስከ አሁን ድረስ በጥላቻ፣ፍጹም በሆነ ራስ ወዳድነት፣በቂም፣ በጨለማ ፣በክፋት ፣በድንቁርና …ትመላለሳለህን… በቤትም በከተማም ያለኸው?



ያገሬ ሰው ሆይ በሕያው እና በእውነተኛው አምላካችን ስም እማጸንሃለሁ ፤ይህን ክፋትህን አሁኑኑ ጣለው።ያረገዝከውን ቂም አስወርደው። ስንፍናህን ተጸየፈው። መከፋፈልህን አሁኑኑ አቁም። ከእንግዲህ እጅ ለእጅ ተያይዘህ ከክርስቶስ ፍቅር ይቅርታን እየተማርክ ፣ከክቡር ማንዴላ ተምሳሌት እየወሰድክ ፤ ከማርቲን ሉተር እስከ ሚስተር ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ያለውን የምህረት፣የእምነት፣የተስፋ ሂደት እያየህ ፤ ከጌታ አምላክህም ፍጹም አንድነትን እየተማርክ ፤መሪ ከሆንክ በሰላም፤በአንድነት ፣በእውነት ፣በእኩልነት ምራ።ተቃዋሚ ከሆንክ መጀመሪያ የራስህን ጉዳት እና ክፍፍል ተቃወም።ተቃውሞህ የምትቃወመውን ለማጥፋት ሳይሆን ፤ሲሆን አንተ ደሞ ስልጣን ይዘህ አገር እንዴት በሰላም፤በእኩልነት ፤ለሕዝቦች የጋራ ብልጽግና በዴሞክራሲ …እንደሚመራ ለማሳየት ፤ሳይሆን ደሞ ሲቀር በበለጸገ ተቃውሞ የገዢውን ፓርቲ መስመር ለማስያዝ ፣ለመምከር ፣ለመገሰጽ ይሁን እንጂ።



ምነው ያገሬ ሰው ሆይ? በሃያ አንድ ሺህ ዘመን እኮ ነው ያለነው።



መሪም የሆንክ በሰላም እኩልነት ምራ። መምራትም ከሰለቸህ ለተቃዋሚዎች ዕድል ስጣቸው።ጠባብ አትሁን።የሁሉ መሪ በሰማይ እንዳለ አይዘንጋህ።የታሪክን ሂደት አትርሳ።ታሪካዊ ስህተተ እንዳትሳሳት።



ተቃዋሚም የሆንክ ለሰላም እኩልነት ለሀገር ብልጽግና ወጥረህ ተቃወም።ጭፍን አትሁን።ዕድል ከእግዚአብሄር ቢሰጥህ ምንድነው የምታደርገው?አንተ ደሞ እናት ሀገርህን በበኩልህ ምን ታደርጋት ይሆን?



በመጨረሻም የምልህ ያገሬ ሰው ሆይ ፤ሰውን ሁሉ ውደድ፣አክብር፣በደልን ይቅር በል።ማንንም አትናቅ።ሰውን የናቀ ፣የሰደበ የሰራውን እግዚአብሄርን እንደናቀ፣እንደሰደበም ነውና -ዋልህ።እግዚአብሔር እንዳይሰድብህ እንዳይንቅህም።በፊቱ ውደቅ ማረኝ በለው።ዋልህ ፣ፍራ።እኔ እንኳ አሁን ይህን ስጽፍልህ እንዴት እየፈራሁ መሰለህ።ይማረን ፣ምህረት ቸርነቱም አይለየን።አሜን።



ይወደናል ፤እንድንወደው ደሞ ይገባዋል።



እንዴ ምነው።



እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ።አሜን።

ዘመድህ ብላቴናው ነኝ።ከሀገረ እንግሊዝ።



ክብር ለዘለዓለም ለስሙ ይሁን።

የካቲት ፪ሺ፬ ዓ.ም
Februray 2012


---

በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።-ትንቢተ ዘካርያስ 4:6
'Not by might nor by power, but by my Spirit,' says the LORD Almighty.- Zechariah 4:6