»

እንደተቀበልኩት ምህረት እንደቸርነትህ ብዛት እንዳገለግልህ እርዳኝ ጌታ ሆይ ስጠኝ የመንፈስን እሳት"-በዚህ ዌብሎግ እውነተኛው የጌታ ኢየሱስ ባሪያ ተስፋዬ ጋቢሶ ይታወስ ዘንድ ወሰንን።This weblog has been dedicated to Tesfaye Gabiso,the faithful servant of The Lord.

Sunday, 14 August 2011

ደክመው አይቷቸው


ደክመው አይቷቸው  መኖር ታክቷቸው
ጥግ ላይ አይቷቸው አይዟችሁ አላቸው።

ወድቀው አይቷቸው አቅም አልቆባቸው
ሲድሁ አይቷቸው ውሃ አጠጣቸው።

ሞተው አይቷቸው መቃብር ቀብሯቸው
ብርሃን ጠፍቶባቸው ጌታ አነቃቸው።

ታስረው አይቷቸው ነሃስ ጠፍንጓቸው
ብረት ጨፍልቋቸው

ክፋት ነግሶባቸው ባርነት ገዝቷቸው
ጌታ አዝኖላቸው
ከዛሬ ጀምሮ ከዛሬ ጀምሮ ከዛሬ ጀምሮ
ነጻ ናችሁ አላቸው።


No comments :

Post a Comment

Comment.Share.ይሳተፉ እንጂ።