»

እንደተቀበልኩት ምህረት እንደቸርነትህ ብዛት እንዳገለግልህ እርዳኝ ጌታ ሆይ ስጠኝ የመንፈስን እሳት"-በዚህ ዌብሎግ እውነተኛው የጌታ ኢየሱስ ባሪያ ተስፋዬ ጋቢሶ ይታወስ ዘንድ ወሰንን።This weblog has been dedicated to Tesfaye Gabiso,the faithful servant of The Lord.

Thursday, 10 November 2011

ሊያፈርስ ተገለጠ

“ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ።” (1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3:9) የሚለው ቃል አሁን እንኳ ቢሆን በዚህች ደቂቃ የታመነ ነው፦

ሞትን ሊያጠፋ ሕይወት ተገለጠ።
ጨለማን ሊያጠፋ ብርሃን ተገለጠ።
ውሸትን ሊያጠፋ እውነት ተገለጠ።
ኩነኔን ሊያጠፋ ጽድቅ ተገለጠ።
ክፋትን ሊያጠፋ በጎነት ተገለጠ።
መጥፋትን ሊያጠፋ መንገድ ተገለጠ።
ብክነትን ሊያጠፋ እረፍት ተገለጠ።
ጥማትን ሊያጠፋ እርካታ ተገለጠ።
ስጋን ሊያጠፋ መንፈስ ተገለጠ።
ገንዘብን ሊያጠፋ አምላክ ተገለጠ።
እንጀራን ሊያጠፋ ቃል ተገለጠ።
ማየትን ሊያጠፋ እምነት ተገለጠ።
ድካምን ሊያጠፋ ብርታት ተገለጠ።
ፍርሃትን ሊያጠፋ ፍቅር ተገለጠ።
ጥላቻን ሊያጠፋ መውደድ ተገለጠ።
ጨለማን ሊያጠፋ ዕውቀት ተገለጠ።
ተስፋቢስነትን ሊያጠፋ ሕያውተስፋ ተገለጠ።
እኔን ሊያጠፋ እኛ ተገለጠ።
መራገምን ሊያጠፋ ባርኮት ተገለጠ።
መሳደብን ሊያጠፋ ምስጋና ተገለጠ።
እርቃንን ሊያጠፋ ጸጋ ተገለጠ።
ጨለማን ሊያጠፋ ውበት ተገለጠ።
ጦርነትን ሊያጠፋ የሰላሙ ንጉስ ተገለጠ።
ሀዘንን ሊያጠፋ ደስታ ተገለጠ።
ዓለምን ሊያጠፋ ኢየሱስ ተገለጠ።

አሜን።

No comments :

Post a Comment

Comment.Share.ይሳተፉ እንጂ።