ማይ ላይፍ ኢዝ ኢን ኤ ሜስ
አይ ዶንት ኢቭን ኖው
ሀው አይ ዊል ጌት አውት ኦፍ ዚስ
ብሎ እያለ ጥቂት ሲቀረው በአያሌው ሊተክዝ
"የሠላሙ አምላክ ከእኔ ጋር ነው
የሠላሙ ንጉስ ከእኔ ጋር ነው
አልታወክም በሚሆነው
አልታወክም ሊሆን ባለው"
የሚል የጥንት ዘመን መዝሙር
ወደ ልቡ ትዝታ ተሰጠው::
***
ሆኖም ቢሆን ግን ለወንድሞች ተግሳጽ ይሆን ዘንድ ብሎ በበጎ ልቡና ከወንድሞችም ፍቅር የተነሳ "...ለዚህ ሁሉ የተዳረኩት..." ሲል ለንስሃ በሚያበቃ የትዝታ ፀፀት መገረፉን ለጉባኤው መደበቅ አልፈለገም:: "...ኣዎና በጸሎት አልተጋሁም ነበርና፣ቃለ እግዚአብሔርን ማንበብ እጅጉን ቸል ብዬ ነበርና፤መጾምን በሰበብ አስባብ፣ በስጋ ድካም ፣በሆዳምነት ...ወዘተ መጾምን አልጾምኩም ነበርና ፤አብዝቶ አገልጋይ ፣ሯጭ ፣ተሯሯጭ ፣ሰባኪ ፣ተናጋሪ ፣ጸሐፊ ፣አንባቢ ሆኜ መታዘዝ ከመስዋዕት ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ ከማቅረብ እንደሚበልጥ መገንዘብ ብቻ ተስኖኝ ነበር እንጂ..."ሲል ለጉባኤው አስረዳ::በጉባኤው መረብ ብዙ ሺህ ሕዝብ ነበር::ሂዝ ሜርሲ ኢንዱረስ ፎር ኤቨር::
ክብር ለስሙ ይሁን::
No comments :
Post a Comment
Comment.Share.ይሳተፉ እንጂ።