እግዚአብሔር ሆይ እንዴት ድንቅ ነህ
ነፍሳችን ረካች በጉብኝትህ
ጥያቄያችንም ተመለሰልን
ስምህ ይባረክ ከፍ ይበልልን
ጠላት ጠፍሮ ፍጹም ተብትቦ
እንዳናመልክህ ዙሪያው ተከቦ
መሰንቆአችንን ከሰቀልንበት
ዛሬ አውርደን ንገስ አልንበት
አዝ….
እኛስ ቆዝመን አዝነን ነበር
ማየት ተስኖን ከሞት ባሻገር
በትንሣኤው ኃይል ደስታን ሞልተኸን
በባዕድ ምድር እንዘምራለን
አዝ….
ከአቻምና አምና ከአምናም ዘንድሮ
ያንተ ቸርነት ስንቱ ተቆጥሮ
ስንቱን ጨለማ አሸጋገርከን
ከምንገምተው በላይ ሆንክልን
አዝ…
...የሚል የጥንት ዘመን መዝሙር ትዝ አለኝ። እባክዎ ይበሉ ይቀጥሉ እርስዎ ይዘምሩ እንጂ።
***
http://www.zimmare.com/song.php?s=s&i=2052a07c
No comments :
Post a Comment
Comment.Share.ይሳተፉ እንጂ።