»

እንደተቀበልኩት ምህረት እንደቸርነትህ ብዛት እንዳገለግልህ እርዳኝ ጌታ ሆይ ስጠኝ የመንፈስን እሳት"-በዚህ ዌብሎግ እውነተኛው የጌታ ኢየሱስ ባሪያ ተስፋዬ ጋቢሶ ይታወስ ዘንድ ወሰንን።This weblog has been dedicated to Tesfaye Gabiso,the faithful servant of The Lord.

Saturday 31 August 2013

ለሌላ ፡ ነገር ፡ መኖር ፡ አይችልም

ሌላ ፡ ነገር ፡ ታገስ ፡ ብትለኝ
ጠብቃለሁ ፡ እስኪሆንልኝ
ግን ፡ አባቴ ፡ ለክብርህ ፡ ነገር
በህልውናህ ፡ ውሎ ፡ ለማደር
አዝ:- ቸኮለብኝ ፡ ልቤ ፡ ሊያገኝህ
እንዴት ፡ ብዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ልያዝህ
ናፍቆቴ ፡ ነህ ፡ የሁሌ ፡ አምሮቴ
አንተን ፡ ማየት ፡ ክብርህ ፡ ጉጉቴ (፪x)

ኢየሱስ ፡ ዓይኔ ፡ በርቶ ፡ አንዴ ፡ ልይህ
ኢየሱስ ፡ ውስጤ ፡ ራበኝ ፡ እስከምነካህ
ኢየሱስ ፡ እኔ ፡ አልችልም ፡ መኖር ፡ ካለዚያ
ኢየሱስ ፡ በሌለበት ፡ ክብርህ ፡ ህልውናህ (፪x)
አዝ:- ቸኮለብኝ ፡ ልቤ ፡ ሊያገኝህ
እንዴት ፡ ብዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ልያዝህ
ናፍቆቴ ፡ ነህ ፡ የሁሌ ፡ አምሮቴ
አንተን ፡ ማየት ፡ ክብርህ ፡ ጉጉቴ (፪x)

አንተን ፡ ማየት ፡ ክብርህ ፡ ጉጉቴ
አባትዬ ፡ ፊትህ ፡ ጉጉቴ
ኢየሱሴ ፡ ክብርህ ፡ ጉጉቴ
አባትዬ ፡ ክብርህ ፡ ኢየሱሴ
ኢየሱሴ ፡ የነካው ፡ ሰው
ኢየሱስን ፡ በዓይኑ ፡ ያየ ፡ ሰው
ኢየሱሴ ፡ የገባው ፡ ሰው
ኢየሱስን ፡ በዓይኑ ፡ ያየ ፡ ሰው
ለሌላ ፡ ነገር ፡ መኖር ፡ አይችልም (፪x)
ለፈለገው ፡ ነገር ፡ መኖር ፡ አይችልም
ለፈለገው ፡ ነገር ፡ መኖር ፡ አይችልም (፪x)

የመቅደስን ፡ ደጅ ፡ የሚጠኑ
ብዙ ፡ ናቸው ፡ አንተን ፡ የሚሹ
አምላክህን ፡ አሳየኝ ፡ ሚሉኝ
ክብሩ ፡ የታል ፡ እስኪ ፡ አሳውቀን

ወዴት ፡ ልበል ፡ የት ፡ ጋር ፡ ነህ ፡ ውዴ
በእኔ ፡ ዘመን ፡ ይረፍ ፡ ትውልዴ
ከእኔ ፡ ውጪ ፡ የትም ፡ አልጠቁም
በእኔ ፡ ላይ ፡ ና ፡ እስኪያይህ ፡ ሁሉም (፪x)
ኢየሱስ ፡ ዐይኔ ፡ በርቶ ፡ አንዴ ፡ ልይህ
ኢየሱስ ፡ ውስጤ ፡ ራበኝ ፡ እስከምነካህ
ኢየሱስ ፡ እኔ ፡ አልችልም ፡ መኖር ፡ ካለዚያ
ኢየሱስ ፡ በሌለበት ፡ ክብርህ ፡ ህልውናህ (፪x)

የጭንቅ ፡ ነው ፡ ስጠራህ ፡ ውዴ
የውስጤን ፡ ምጥ ፡ ቃላት ፡ ሰብስቤ
ቢነግርልኝ ፡ የልቤን ፡ ጩኸት
የጥማቴን ፡ የርሃቤን ፡ ልክ

እስከመቼ ፡ እንዲሁ ፡ በልማድ
ያሰለቻል ፡ ሲደገም ፡ ትላንት
ብዙ ፡ ክብር ፡ ብዙ ፡ ህልውና
አዲስነት ፡ በየማለዳ (፪x)
ኢየሱሴ ፡ የነካው ፡ ሰው
ኢየሱስን ፡ በዓይኑ ፡ ያየ ፡ ሰው
ኢየሱሴ ፡ የገባው ፡ ሰው
ኢየሱስን ፡ በዓይኑ ፡ ያየ ፡ ሰው
ለሌላ ፡ ነገር ፡ መኖር ፡ አይችልም (፪x)
ለፈለገው ፡ ነገር ፡ መኖር ፡ አይችልም
ለፈለገው ፡ ነገር ፡ መኖር ፡ አይችልም (፪x)


Mezmur Lyrics at WikiMezmur.org http://wikimezmur.org/am/Yidnekachew_Teka/Chekolebegn/Chekolebegn_Lebie#ixzz2U0yf9Ocd