ኧረ እኔ ማነኝ ቤቴስ ምንድነው
ከጣሪያዬ በታች ኢየሱስ የገባው (2)
ምህረት የበዛለት ፍቅር ይቅር ያለው
ደሞ ያየ ቸርነቱን እንደኔ ያለ ማነው (2) ...
(እኔማ) ሞተ ስባል ያለሁ
(እኔማ) ጠፋ ስባል የቆምኩ
(እኔማ) ምንም እንዳላየ
(እኔማ) እንዴት ዝም እላለሁ
(እኔማ) እኔማ ስላንተ
(እኔማ) ለሀገር ለምድሩ
(እኔማ) አልጠግብ አውርቼ
(እኔማ) ምህረት አግኝቼ
ምህረት የበዛለት...
በምህረትህ ብዛት ቤትህ እገባለሁ
አንተ ራርተህልኝ እኔም ሰው ሆኛለሁ (2)
አቤቱ የወደቀውን እንዴት አየኸው
አቤቱ የተረሳውን እንዴት አሰብከው
ምህረትህ ምህረትህ እጅግ ብዙ ነው
ፍቅርህ ፍቅርህ እጅግ ብዙ ነው (2)
አቤቱ ታናሹን ሰው እንዴት አየኸው
አቤቱ የተጠላውን እንዴት ወደድከው
ምህረትህ ምህረትህ እጅግ ብዙ
ነው ፍቅርህ ፍቅርህ እጅግ ብዙ ነው (2)
(እኔማ) ያንን ዘመን ሳስብ
(እኔማ) እንባ ይቀድመኛል
(እኔማ) ሞት ሽረት ሆኖብኝ
(እኔማ) ማን አለሁ ብሎኛል
(እኔማ) ከበለሱም በታች
(እኔማ) ድምፅህን መስማቴ
(እኔማ) ያ ነው ሰው ያረገኝ
(እኔማ) የመኖር ምክንያቴ
ምህረት የበዛለት...
***
Lyrics source:http://www.zimmare.com/song.php?s=s&i=64369270
No comments :
Post a Comment
Comment.Share.ይሳተፉ እንጂ።