»

እንደተቀበልኩት ምህረት እንደቸርነትህ ብዛት እንዳገለግልህ እርዳኝ ጌታ ሆይ ስጠኝ የመንፈስን እሳት"-በዚህ ዌብሎግ እውነተኛው የጌታ ኢየሱስ ባሪያ ተስፋዬ ጋቢሶ ይታወስ ዘንድ ወሰንን።This weblog has been dedicated to Tesfaye Gabiso,the faithful servant of The Lord.

Saturday, 7 December 2013

በአንድ ወፍ ሁለት ድንጋይ ላይ ሳርፍ።

ከአፈር ከጭቃ አንስተኸኝ በሁለት እግሮቼ ያቆምከኝ

  • ልምምድ ፩፪

በጌታ ፍቅር የሚወዱኝ ዘመድዎ  ድንገት ሳላስበው ውጥን ሳይኖረኝ  አፈር ከጭቃ አንስተኸኝ የተሰኘውን መዝሙር ከዘመርኩበት ካለፈው ሳምንት ዠምሮ ዛሬም እየዘመርኩ አለሁ ዘንድሮ


  • ልምምድ ፲



ኪይቦርድ የሚሉትን የሙዚቃ መሳሪያ እየተማርኩ ስላለሁ ለምን ከአፈር ከጭቃ የሚለው መዝሙር በኪቦርድ ሁናቴው ምን ሊመስል እንደሚችል  አላጤነውም ብዬ ልቤ ድንገት አስቤው ተነሳሳ

በመዠመሪያ ስዊንግ እና ጃዝ መስሎኝ ብዙ ለፋሁና አልሆን ሲለኝ ጊዜ ይህ ነገር ባላድ ይሆን እንዴ ብዬ ወደ ባላድ ሄድኩኝ።ባላድ አታለለኝ።ላካንስ የሚያታልል ነገር መዠሪያ ላይ የማያታልል ነው የሚመስለው

ልቤ ግን ነግሮኝ ነበር አልሰማም ብዬ ነው - እንደ ፈረስ ጉዞ ያለ ሶምሶማ ሊሆን እንደሚችል

አሁን ገና ደረስኩበት ብዬ ወደ ካንትሪ ሄድኩኝ።ካንትሪ በግልጽ ነው የነገረኝ - ሂድ ከዚህ ሂድልን ከዚህ በፊት ብዙ ተሳክቶልሃል ለዛሬ ግን አልተሳካልህም አምልጥ አለኝ አልተከራከርኩም

የሚራመድ ሰው ነው ላካስ ተጓዥ ሰው ሁለት ሶስቴ ወደፊት እየሮጠ (የሚሮጥ እየመሰለ)ወይስ በእውን እየሮጠ ነው አይታወቅም አየሮጠ የሚቆም የሚመስል ሰው

አለብን ሶምሶማ።
***
አርስዎ የምወድዎት ዘመዴ ታዲያ ክፋት የሌለው ጨዋታ ስለሚወዱ እነ ልምምድ ፩ ፣፪ ፣፫ ፣፬፣፮... ወዘተ የታሉ ብለው ፈታኝ ጥያቄ እንዳይጠይቁኝ ። የግድ የግድ መልስ ይሰጥ ከተባለ ግን እነርሱ እራሳቸው ለምን እየጠየቁም ብዬ  እንዴት ያለ ሰላማዊ ብስጭት እንዳበሳጩኝ ትዝ እያለኝ ሳያቸው ለካንስ ወደ ኢንተርኔትም ይሁን ወደ ዩቲዩቭ አንጓዝም ብለው አስፈቅደው ኖሯል

ጌታ ይመስገን።

No comments :

Post a Comment

Comment.Share.ይሳተፉ እንጂ።