»

እንደተቀበልኩት ምህረት እንደቸርነትህ ብዛት እንዳገለግልህ እርዳኝ ጌታ ሆይ ስጠኝ የመንፈስን እሳት"-በዚህ ዌብሎግ እውነተኛው የጌታ ኢየሱስ ባሪያ ተስፋዬ ጋቢሶ ይታወስ ዘንድ ወሰንን።This weblog has been dedicated to Tesfaye Gabiso,the faithful servant of The Lord.

Sunday, 8 December 2013

አምላኬ ታማኝ ነው በመንገዱ

Hewane Luv & Life Gardens » Song of the Week »

ለገሠ ወተሮ
አምላኬ ታማኝ ነው በመንገዱ


አምላኬ ታማኝ ነው በመንገዱ (4)

በሐሩር ያሸዋ በረሃ ወይን አቆጠቆጠ
ጌታ በቃሉ ያለው ተፈፀመ
ቃሉ አይደክምምና በታላቁ ክንዱ ይሠራል
ለበረሃው ልብህ ፍሬ ይሰጣል
አዝ…

የሞተው ሁሉ ሲነሣ የማይሞት አካል ለብሶ
መበስበስ ላያይ ዳግም ተመልሶ
በዕድሜው ያፈራውን ሰው ሁሉ ያንኑ ያቀርባለ
ለጌታ የሚሆን ምን መከራ ይዘሃል
አዝ…

ከሥጋህ ነው ያጨድከው ወይስ ከርሱ ቅዱስ መንፈስ
ለሕይወት ይሆን ወይስ ለመበስበስ
መንገድህን አሁን ቀይር ፍሬህም አይቅር መና
የምሕረት ጊዜ አላለቀምና
አዝ…

ቢመስልህ ላንተ የተነፈገህ ደሞዝህ ዛሬ
ለድካምህ መኖ ለለቅሶህ ፍሬ
ታገል አትፍራ በርታ ጌታ አምላክህ ይረዳሃል
ለድካምህ አንድ ቀን አክሊል ይሰጣል
አዝ…

____
If you know where to find the video/audio,please advise.
Hewane Poetry Song of the Week Department.
With thanks.

No comments :

Post a Comment

Comment.Share.ይሳተፉ እንጂ።