»

እንደተቀበልኩት ምህረት እንደቸርነትህ ብዛት እንዳገለግልህ እርዳኝ ጌታ ሆይ ስጠኝ የመንፈስን እሳት"-በዚህ ዌብሎግ እውነተኛው የጌታ ኢየሱስ ባሪያ ተስፋዬ ጋቢሶ ይታወስ ዘንድ ወሰንን።This weblog has been dedicated to Tesfaye Gabiso,the faithful servant of The Lord.

Tuesday, 11 February 2014

በእግዚአብሔርም ቤት ለዘለዓለም እኖራለሁ።

እግዚአብሔር እረኛዬ ነው
የሚያሳጣኝም የለም
በለመለመ መስክ ያሳድረኛል
በእረፍት ውሃ ዘንድ ይመራኛል
ነፍሴን መለሳት
ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ
በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ
አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም
በትርህና ምርኩዝህ እነርሱ ያጽናኑኛል
በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ
በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ
ጽዋዬም የተረፈ ነው
ቸርነትህና ምህረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል
በእግዚአብሔርም ቤት ለዘለዓለም እኖራለሁ።

No comments :

Post a Comment

Comment.Share.ይሳተፉ እንጂ።