»

እንደተቀበልኩት ምህረት እንደቸርነትህ ብዛት እንዳገለግልህ እርዳኝ ጌታ ሆይ ስጠኝ የመንፈስን እሳት"-በዚህ ዌብሎግ እውነተኛው የጌታ ኢየሱስ ባሪያ ተስፋዬ ጋቢሶ ይታወስ ዘንድ ወሰንን።This weblog has been dedicated to Tesfaye Gabiso,the faithful servant of The Lord.

Thursday, 13 January 2011

አሳ።ባሕር።ሕይወት።

እኔ አሳ አይደለሁምን?
ውሃውስ ህይወቴ አይደለምን? ከውቅያኖሱ ቤቴ ከወጣሁ በአየር-ጥማት ታፍኜ -ጥቂት ተፍ ተፍ ብዬ ክንብል ማለቴ ነው እንጂ።

እንኳን ከውሃው ህይወቴ ወደ የብስ በረሃው ወጥቼ እንዲያዉም አዳኝ ወፎ ች አሰፍስፈው ይከታተሉኛል ሊውጡኝ።አንዳች የሰማይ ንስር ይዋጣቸው።

እኔ አሳ ሆኜ እንደምን በውሃ አፍራለሁ?

ውሃዬ ሕይወቴ ሆይ ይቅር ብለህ በውቅያኖሱ ግዛትህ አኑረኝ እልፋለም።

ክብር ለስምህ።

No comments :

Post a Comment

Comment.Share.ይሳተፉ እንጂ።