»

እንደተቀበልኩት ምህረት እንደቸርነትህ ብዛት እንዳገለግልህ እርዳኝ ጌታ ሆይ ስጠኝ የመንፈስን እሳት"-በዚህ ዌብሎግ እውነተኛው የጌታ ኢየሱስ ባሪያ ተስፋዬ ጋቢሶ ይታወስ ዘንድ ወሰንን።This weblog has been dedicated to Tesfaye Gabiso,the faithful servant of The Lord.

Saturday, 11 June 2011

የኛ ሰው በሰማይ


ሰዎች ሁሉ በመልከ እንጀራ
የሚራቡህ ረሀብ
በአምሳለ ውሃ የሚጠሙህ ጥማት
ተረዳን ዛሬ አንተ  እንደሆንክ

ሰዎች ሁሉ የሚራቡት ፍቅር
አንተ ነህ
ሰዎች ሁሉ የሚረኩት ፍቅር አንተ ነህ

ሰዎች ሁሉ የሚዋቡት ውበት
የሚጠሙት ጥማት አንተ ነህ

ሰዎች  ሁሉ የሚናፍቁት ሰላም
እረፍትና ምህረት
አንተ ነህ።

እልፍ ቢሉ ይህን ሁሉ እንደሆነው
ሆኖ ያገኙታል
ከዚያም ቀን ጀምሮ መኖርን ይጠሉታል።
እስከዚያው ግን የራሳቸውን መኖር ይኖሩታል።

የመለኮት ምርጫ ዕድል ጉዳይ እንደሆን
ጥርጥር የለውም አሁን በዚህ ሰፈር
ኋላ ላይ ግን ለሁሉም ነው
በሚመጣው ሰፈር።

የእግዚአብሔር ልጅ።

No comments :

Post a Comment

Comment.Share.ይሳተፉ እንጂ።