ያመለጥኩ መስሎኝ ነበር አሉ ጋሽዬ?
ምን እናደርጋለን እንግዲህ -ከመሰሎት።
ግድ የሎትም ይቆዩ ጋሽዬ።
***
አንት አያሌው ምን ሆነህ ነው?
ከስክስ በበጋው አጥልቀህ ቤተስኪያን የተጓዝከው?
ወንጌል ማንበብ አቁመሃል ብለን እንፍራ?የሰላም ጫማ አድርጉ መባልን አንተ በከስክስ ተገነዘብከው?
ይሁን የኛው ነህ የትም አታመልጥም።
ዳሩ ግን በከስክስ ጫማህ የብዙ እህቶችን እግር እንደከሰከስክ ሰምተናል።
ሳላውቅ ነው ትላለህ።
ሳያውቁ የሰው እግር መከስከስ ስንት ይፈጃል?
ና፤ልታናግረን ይገባል።የኛው ነህ የትም አታመልጥም።እንኮረኩምሃለን-ከፈቀድክልን።
እሁድ ከአምልኮ በኋላ ፓስተር ሊያናግሩህ ይሻሉ።
ብትቀር እንኳን እንዳትቀር።የትም አታመልጥም።እንጎበኝሃለን።
ባትቀር እንጂ ብትቀር አያዋጣህም።
***
እታለም አሁድ ‘ለት አየንሽ።
ስፒል ጫማ አጥልቀሽ በዕለተ ሰንበት ቤተስኪያን ውስጥ?
ይሁን የኛው ነሽ።
ከኋላ ረድፍ ትቀመጣለች ብለን ስንገምት አንቺ ሆይ አሳሳትሽን-በስፒሉ ጫማሽ ወለሉን እያስቆጣሽው እፊት ድረስ ገሰገስሽልን።
እኛም በልባችን ስፒሉንስ ታድርገው ከወደደች -ግን ምን አለበት ከኋላ ረድፍ ብትሰየም ብለን ልናስብ ጥቂት ሲቀረን ፤ገና እንደተቀመጥሽ ስፒሉን ጫማሽን አውልቀሽ፣በንጹህ ውሃ የታጠቡ እግሮችሽን ወለሉ ላይ ስታሳርፊው ስናይ በዚያም ላይ አክለሽ መንፈስሽን-ሰብሰብ፣አካልሽን -ጭምት ፣ራስሽን-ደፋ አድርገሽ በፍቅረ-ወንጌል ሻሽ የተሸፈነውን ጸጉርሽን ዘንፈል አድርገሽ ፤ለአምልኮ፣ለክብሩም ምስጋና ራስሽን ዝቅ ስታደርጊው ስናይ እጅጉን ደስ ተሰኘን።
የኛ ናት!ብለን በልባችን ጮህን።
የኛ የራሳችን -የቤተክርስቲያን ልጅ ነች አልንልሽ በሀሳባችን።
እውነቱን እነግርሻለሁ የዚያን ዕለት ስፒል ጫማ ማድረግሽን ያስታወሰ እስካሁን አልተገኘም።
ሆኖም ቢሆን ግን ፓስተር ኋላ ላይ ሊያናግሩሽ ይፈልጋሉ።
***
ያምልጡ።
ካመለጡ ያስመልጡ።
***
‘ይቆዩ ጋሽዬ’ አልከኝ አንተ ወጣት?
መቸም ሰው አክባሪ ነህ -አንድዬ ያክብርህ።
ሆኖም ቢሆን ግን ስለምንድነው መቆየት የተገባኝ?
አዎን ጋሽዬ ማምለጥ አለብዎት።
የግድ አምልጥ ካልከኝ አንተ ወጣት ልጅ ፤
ከምንድነው የማመልጠው?
ወዴትስ ነው የማመልጠው?
እንዴትስ ነው የማመልጠው?
አምልጥ -አምልጥ ትለኛለህና አንተ ወጣት -ልቤን ልታሸብር ምንም አልቀረህም።
አምልጥ፣ያምልጡ በሚል አበሳ
ድልድል ልቤን አራድከውሳ።
ጋሽዬ እንደሱ አይደለም ማለት፤እንደሱ ነው እንጂ።
ውንብድናዋን እንኳን ለኛ ተዋት።አይደለም እያልከኝ ነው ደሞ ትለኛለህ- ወጣት?
ጋሽዬ እሱን እኮ ነው የምሎት -ተወናብደናል።
ውንብድና አግኝቶሃል እያልከኝ ነው አንተ ልጅ?
ውይ ጋሽዬ በምን አቅሜ?እንዴትስ ደፍሬ?ያልኩት ግን አንዳች ክፉ ውንብድና ገብቶ አወናብዶናል እንጂ።
ከማላየው ከማላውቀው ውንብድና እንዴት ማምለጥ ይቻለኛል ብልህስ?
ጋሽዬ ውንብድና ባለበት ሁሉ ወይ ወንበዴ አለ ወይም ነበር።አንዳች ክፉ ውንብድና በመልካሙ እርሻችን ወንበዴ ዘርቶብን አልፏል ብዬ ብፈራስ-ጋሽዬ?
እንዲህ ያለ ነገር እኮ ከሰማን ቆየን አንተ ልጅ።
እንዲያው ላንተ ስል -እንዳላሳፍርህ ላምልጥ ብል እንኳ -ከወንበዴው ነው ወይስ ከውንብድና ነው የማመልጠው?
ጋሽዬ እርስዎ የተባረኩ ሰው እኮ ነዎት።
እየውሎት ወንበዴውን ፖሊስ የገባበት ገብቶ በነሐስ የዘላለማዊ ሰንሰለት አስሮታል።
ወንበዴው የዘራው የውንብድና ዘር ግን እስከ አሁን ድረስ አልፎ አልፎ እያወናበደ ስለሆነ ከእርስዎ የሚጠበቀው ፦
ሀ) ውንብድናን “ውሸት”
ለ) “እውነትን” እውነት ማለት።
ይህን እውነት ቢያምኑ በልብዎ
ባደባባይ ቢመሰክሩ ደሞ
እስር አይጣሉም
አምልጠዋልና እርስዎ።
***
አያሌው መጣህልን?በል ግባ እስኪ።
ለመሆኑ ስለምን ኖሯል የእህቶችን እግር በከስክስ ጫማህ ያቆሳሰልከው?
አሰናክለውኝ ነው ፓስተርዬ።
ማሰናከል የሚለው ቃል ምን እንደሆነ ብታውቅ አትጠቀመውም ነበር።ይሁን - ወጣት ነህ።እንዴት ነው ግን ያሰናከሉህ?
እኔ ስመጣ ይመጣሉ እኔ ስቀር ይቀራሉ።
እ ...አንተው እራስህ ኖረሃላ?
ምኑ ፓስተር?
ስለሌሎች የምትለውን የምታደርገው?
እ...
እህቶችን ልመጎብኘት ብለህ ኖሯዋላ ቤተስኪያን የምትመጣው?
አላረገውም!
ከእንግዲህ?
እረ ጥንትም አላረ...እ
አይዞህ የኛው ነህ።አትጨነቅ።አታስጨንቅ።
ታሁን ኋላ ተገቢውን ጫማ አጥልቅ።
ፍቅረ-ወንጌልንም ዞትር አንብብ።
ጾመህ ታውቃለህ ግን አያሌው?
ፓስተር እንዴት መሰሎት ..እ...ባይብል እንደሚለው...
አይዞህ የኛው ነህ።አትጨነቅ።ወይ አያሌው ወጣቱ እንዴት እንደምንወድህ ብታውቅ በምንም አትጨነቅም ነበር።
የኛው ነህ።
ካሁን ኋላ እግሮችህ ማስተዋልን ያግኙልህ።ከስክስ ጫማህን በአንዴ አውለቀህ ጣለው አንልህም።እራስህ በሂደት ትቀይረዋለህ።
የምታሰናክልህም ወይዘሪት ካለች ፤ና አማክረን።እንድትወያዩ እንደርጋለን።ከሁሉ በላይ እና በፊት ደግሞ እንጸልይልሃለን።አጥርተህ ትራመድ ዘንድ ይረዳሃል።በነገር ሁሉ በጥቂቱም በብዙም ጸሎት ማሳረግ ጌታን ማክበር ነውና ፤ደሞስ ጸሎት የተጋረደን አይን ይከፍታል፣የተሰወረን ልቡና ያበራል፤የታሰሩ እጆችን ይፈታል፣ተዘምሯል ደግሞ...
...የነሐሱን ደጆች ይሰብራል
ደዌና ሕማምን ይሽራል...
ነውና ስለዚህ።
ጤና ታገኛለህ።
ንጹህና ተገቢውን ጫማ አጥልቀህ ቤተክርስቶስ መምጣትህን እስካላቆምክ ድረስ- አያሌው ተወዳጁ ወንድማችን- እጅጉን አምልጠሃል።
ነውና።
ነህና የኛ የትም አታመልጥም።
***
ምን ልቅዳልሽ እታለም?
አይ ሻይ ቡና ብዬ ነው የመጣሁት ፓስተር።
እስቲ እንጸልይ፤እናመስግንም ደግሞ።
አሜን።
ንገሪኝ እንግዲህ።
ከየቱ ልጀምር ፓስተር።
ከአያሌው ጀምሪ።በከስክሱ ጨፍልቆኛል ብለሽ ለኳየር ሊቀመንበራችሁ ነግረሻል።
ስለሱ ልጅ...እ ስለሱ ወንድም ፓስተር ባላወራ ይበጀኛል።
ብታወሪ ይረባሻል- ከወደድሽ።ምንድነው በመሀከላቹ ያለው እሳት ነው ውሃ?
እ...አልገባኝም ፓስተር።
እሱ ታሰናክለኛለች ይላል።አንቺ ደሞ በከስክሱ ይሁነኝ ብሎ ረገጥ አድርጎኝ ያልፋል ትያለሽ።ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ድብብቆሽ የለም።ተሳሰባችሁ ወይ?
ውይ ፓስተር እርስዎ ሲበዛ ግልጽ እና ቀጥተኛ ነዎት።ልቤን ሳታስበው አስደንገጧት እኮ።
ከቤቱ ነው።
እ..አልገባኝም ፓስተር...ከቤቱ ሲሉ?
ግልጽነት እና ቀጥተኛነት ከቤቱ ባለቤት የተወረሰ ነው።እርሱም እራሱ የታላቁ ካህናችን አገልግሎት ነው-የዉሃት እና ቀናነት።ግልጽነታችን እና የዋህነታችን እንዳይጎዳን ደግሞ -በዚህ ክፉ አለም ሳለን-ጥበብ እና ማስተዋልን ከሰማያት እንለምናለን።
እታለም ወጣት ነሽ፤አያሌውም ጎበዝ።
የቀረው ሂደት ነው።በክርስቶስ ጥላ ውስጥ ናችሁና ሰላም ነው።አሰባችሁበት መልካም ቦታ ትደርሳላቹ።
ነውና።
ብቻ ነገን ጎትተን ዛሬ ላይ ለማምጣት ብንላላጥ ፤የተያያዝነው የነግ-ዛሬ ጉተታ ስበት ውጥረተ-ኃይል አስፈንጥሮ ትላንት ላይ እንዳይጥለን እንጸልይ።
ትላንት ከወደቁ ዛሬ ላይ ለመድረስ የሚደረገው ግስገሳ ዳገት ነው።
ለመሆኑ አያሌው ወንድማችን እናንተ ኳየር ለመግባት መውደዱን ሰምተሻል?
ከቶም ቢሆን-ፓስተር።እሱ ኳየር ከገባ እኔ...
ደስ ይልሻልና።ነውና?
እረ ፓስተር እኔ ...
ይሁን።
የቤተክርስቲያናችን የወጣቶች እንቅስቃሴ ማናጀር ከኳየር መሪያችሁ ጋር በመትጋት በምክር እና በጸሎት፣ በትዕግስት እና በትምህርት በተግሳጽ ሁሉ ያግዛችኋል።
እርሷን እና እርሱን አናግሯዋቸው።ሰላም ሁኑ ፤ተከናወኑ።
እሺ ፓስተር ጌታ ኢየሱስ ይባርኮት።
***
ከመሄድሽ በፊት እ...ይሄ የቆምሽበት ምንድነው ስሙ...?ታኮ ጫማ ነው የሚባለው...?ጥሩ ጠንካራ ጫማ ይመስላል ግና ማምለጥ ከደረሰብሽ ይጠቅምሻል ወይስ አይጠቅምሽም?
ፓስተርዬ እኔ እኮ ኦልሬዲ አምልጫለሁ።?
የተደናበረ በሬ ከተማ ውስጥ ሊኖር ይችላል።
ውይ እኔ በሬ አልፈራም ፓስተር።
እንደስፓኛ ተዋጊ በሬ ያለ ቧልተኛ ኮርማ ቢያጋጥምሽስ?ምን ያህላል፣ሲያስፈራ...እያልሽ ጥግ ጥግሽን ይዘሽ ተጠንቅቀሽ ስትጓዢ ታኮ ጫማሽ ጥርጊያውን እየቆፈረ የሚፈጥረው ረገጣ ፤የቧልተኛውን ኮርማ ቀልብ ቢስብስ “ናልኛ እዚ አለሁልና ሞክረኛ” የሚል ቧልታዊ ግብዣ መስሎት ድንገት ቢረብሽሽስ?
እታለም ሆይ ማምለጥስ እውን አምልጠሻል ካመለጥሽው ማምለጥ ብቻ ይቀርሻል እንጂ።
ነውና።?
*** ***
ጌታ ሆይ ፍቅርህ እና ማዳንህ አይከለከልም።
ቃልህም አይታሰርም።
ፈቃድህን ሊያፍኑ የሞከሩ እርኩሳን መናፍስትን እና የሲኦልን ልጆች ሴራ ሁሉ አምክነህ ፤አህጉር ፣አገር፣ስጋ፣ደም ፣ድካም ፣ብርታት፣ ምንም፣ማንም ሳያግድህ ማዳንህን ስለገለጽክ ጌታ ሆይ ዘላለማዊ ክብር ምስጋና ለአንተ እናቀርባለን።
ዘለዓለም እናመሰግንሃለን።
አሜን።
*** ***
...እሺ ስለነበረን ጊዜ ሁሉ ጌታን ኢየሱስን እናመሰግናለን።ያለእርሱ በጎ ፈቃድ አንዳች አይሆንምና።
ፓስተርንም ጌታ ኢየሱስ ይባርካቸው የጌታን የኢየሱስን የበጎ ወንጌል መልእክት ሳላካፈሉን ።እንዲሁ ዘወትር እየመጡ እንዲያገለግሉን የሚያገለግሉት ጌታ በብዙ ምህረት ቸርነቱ ፣በዘላለማዊ ፍቅሩም ይደግፋቸው ።
ጉባኤው በሙሉ እጆቹን በሳቸው አንጻር ወደሰማይ ዘርግቶ ...ጌታ አምላክ አብዝቶ ይባርካቸው።ይጠብቃቸው ፤ይደግፋቸው ይላል።
አሜን።
***
እሺ ..እ....ከአምልኮ መሪዎች ጋር አመለጥኩኝ የሚለውን እየዘመርን ሶሎ ዘማሪዋ እህታችን እታለም ከበገና ተጫዋቹ ወንድማችን አያሌው ጋር የመጨረሻውን መዝሙራቸውን ሊያቀርቡልን ይታደማሉ።
አመለጥኩኝ...
...እጄን ይዞኝ...
እንላለን...እንዘምራለን እነርሱ በገናቸውን እስኪቃኙ።
።
***
ክብር ምስጋና ከዘለዓለም ዓለም እስከዘለዓለም ዓለም ሁሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ይሁን።
ለክብሩም ምስጋና ይሁን።አሜን።
ነውና።
_________
በሰላም ሂዱ....ሳምንቱ የሰላም የደስታ ይሁንላቹ...
*** *** ***
እኛም በክርስቶስ ፍጹም የሚሆን ሰውን ሁሉ እናቀርብ ዘንድ ሰውን ሁሉ እየገሠጽን ሰውንም ሁሉ በጥበብ ሁሉ እያስተማርን የምንሰብከው እርሱ ነው።-ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1:28
*** *** ***
___________________________________
September 2012.
Elias Aldada

No comments :
Post a Comment
Comment.Share.ይሳተፉ እንጂ።