እንኳን በደግ መጡ።
የአምላክ ሰላም እና ጸጋ ይብዛልዎት::
ከጌታ ኢየሱስ ምህረት ቸርነት ጋር በመተባበር ያዘጋጀንልዎትን ገበታ ያንሱ፤ይቋደሱ።
በሻይ ቡና መጀመር ይችላሉ።(እንድየ በዚህ ሰዓት እንዲህ ያለ ግብዣ እንዴት በሻይ ቡና ይጀመራል?) ካሉ ፤ደግ ብለዋል።
እንግዲያው የሚያነቃ፣ የሚያሰክር መጠጥ ፈልገው ኖሯል?ለሰው እንዳይነግሩብን እንጂ እንዲያ ያለውም መጠጥ የስካር ልምድ ላላቸው ብቻ ተዘጋጅቷል። ወደ ጓዳ እልፍ ይበሉ-በዝግታ።
አካሄዶን እና አኳኋኖን አይተን የስካር ልምድ ያሎት ካልመሰለን አናስተናግድም።ወደ አዳራሽ እንመልሶታለን።
እንዴ ምንው ቁመዋል እርሶ?
አትክልት ነው የሚወዱት እርስዎ?እኒህ ተምረናል የሚሉት እና ፈረንጆቹ አገር የሚኖሩት ያገራችን ሰዎች እንደሚነግሩን እርስዎ ቬጂቴሪያኒያን ሮረዋላ?ኋላስ?ተርቤ ልመለስ ነው ብለው አይደንግጡ።ለርስዎም የሚሆን በአቮካዶ የተሰራ የፈረንጅ ወጥ አለልዎት።በዳቦ ከወደዱ ደሞ በእንጀራ -ነጻነትዎ ነው።
አንተ ወንድማችን!እኔ ጂም ሂያጅ ነኝ፣ስፖርተኛ ነኝ፣ሯጭ ነኝ(የት እንደምትሮጥ ግና አልነገርከንም ) ፣የወደፊቱ ኦልምፒክ ሁሉ ከፊቴ አለብኝ የምትለው ፣ይህን ሁሉ የምትነግረን ፕሮቲን ያላነሰበት፣ስብም ያልታጣበት ሁነኛ ገበታ ያሻኛል ፣ቅድሚያም ይሰጠኝ ለማለት ፈልገህ ነው?
ምን ሆነሃል?የጎበዝ ነገር።
ና በወዲህ እልፍ በል፣የረጅም ርቀት ሯጮች ወደሚመገቡበት ማዕድ እናሳልፍሃለን።
እኔ ብዙም እህል አይበላልኝም አልሽ እህታችን።ውነትሽን ነው ወይ?
እንዳትጎጂብን እባክሽ።አይ ፊት ለመሆን ፈልጌ ነው ፤ስራ ቦታ ሁሉም ፊት ናቸው ካልሽ ፤እኛ የግድ እንልሻለን -ስራ ቦታ ብቻ ፊት የሆኑ ቤተስኪያን ውስጥ ኋላም አልተገኙም እና እባካሽ።
ፊትነት በብላት ይሁን ለማለት ነው እንጂ።አንቺ እህታችን - ደሞ የግድ መመረጥ ካለበት -
" የቤተሰብ ብላት
አይልቅም ወይ ከመንደር ፊትነት?"
ስንል ዘረፍንልሽ።
ጋሽዬ ምነው?
ተቤቴ ስወጣ በልቼ ነው የወጣሁት አሉን?ሁሌስ እዲህ ይላሉ እንዴ እርሥዎ? ረጅም ዘመን እኮ አለፍዎት ፍሬሽ ምግብ ሳይበሉ። ጾም ካልሆነ ወዲያ እንጀራ ዘወትር በቀይ ወጥ ብቻ?ምነው?
እንጀራ በዘወትር ቀይ ወጥ አለልዎት ፤አይፍሩ። እኛ ግን የተመኘንልዎት ገበታ ለርስዎ ለየት ይላል።
እኮ እንዴት ያለ ነው?
ደስ ይበልዎት ጋሽዬ ፤ ሲጀምር ገና በቀይ ቪኖ ነው የተጠበሰው::
እ..አላችሁ?
በአዲስ ምድጃ ፤በከሰል ፍም ፤በለስላሳ የጸሐያማው ወራት ጮራ ፍንጣቂ የበሰለ ፣ያረጀ የወይን ጠጅም ያልታጣበት ፤ስብም በጥቂቱ ፤ፍሪምባም ያለበት የቤት ልጆች ናቸው ያዘጋጁት።
***
ለቀጣይ ስመጣ ወዳጅ ዘመድ ይዤ መምጣት እችላለሁን?
እጅጉን።
(share with friends)
***
Foundation:
...እኛም በክርስቶስ ፍጹም የሚሆን ሰውን ሁሉ እናቀርብ ዘንድ ሰውን ሁሉ እየገሠጽን ሰውንም ሁሉ በጥበብ ሁሉ እያስተማርን የምንሰብከው እርሱ ነው::-ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1:28

No comments :
Post a Comment
Comment.Share.ይሳተፉ እንጂ።