ለምን
ወደድከኝ አልልህም በእርግጥ ወደሀኛል
የፍቅርህ
መግለጫ ይሄ ነው ለኔ ተወግተሃል
አንተ
ለኔ የሆንከውን ያህል እኔ ላንተ አልሆንኩም
ምን
ያህል እንደሆን አላውቅም ለክቼ አላየሁም
ግን
አንድ ነገር አውቃለሁ
ስለወደድከኝ
ወድሃለሁ
ከእርግማን ስለዋጀኸኝ ሞተህ ሸክሜን ስለወሰድክ
ከእርግማን ስለዋጀኸኝ ሞተህ ሸክሜን ስለወሰድክ
በመንፈስ
ቅዱስ ስለሞላኸኝ ነፍሴን ስለባረክ
ጸጋህን
አብዝተህ ስለሰጠኸኝ ከቶም ስላልተውከኝ
ምን
ያህል እንደሆን አላውቅም ለክቼ አላየሁም
ግን
አንድ ነገር አውቃለሁ
ስለወደድከኝ
ወድሃለሁ
ደስ
ላሰኝህ እቀናለሁ በህይወቴ ላከብርህ
ሆኖም
ከቶ አልጠቀምኩህም ሁሌ ሳሳዝንህ
ይልቅ
ብዙ አድክሜሃለሁ የትም እየቀረሁኝ
ብዙ ስላላፈራሁ ኢየሱስ ከፍቶኝ አልቅሳለሁኝ
***
ክብር ለዘለዓለም ክብር ለስሙ።
No comments :
Post a Comment
Comment.Share.ይሳተፉ እንጂ።