»

እንደተቀበልኩት ምህረት እንደቸርነትህ ብዛት እንዳገለግልህ እርዳኝ ጌታ ሆይ ስጠኝ የመንፈስን እሳት"-በዚህ ዌብሎግ እውነተኛው የጌታ ኢየሱስ ባሪያ ተስፋዬ ጋቢሶ ይታወስ ዘንድ ወሰንን።This weblog has been dedicated to Tesfaye Gabiso,the faithful servant of The Lord.

Sunday, 6 February 2011

ምጥን የፍቅር ሕይወት ታሪክ

፩.ሰውም ከእግዚአብሔር ጋር በፍቅር ይኖር ዘንድ ተፈጠረ።
፪.ሰውም ተደናበረ።
፫. አዛምዶ ይቀኘው ተብሎም ፍቅር በምሳሌ ሔዋን በብርሌ ተጨመረ።
፬.ሰውም ይልቁን ሰክሮ ተደናበረ።
፭ .ሰውም በምሳሌ ተሰናከለ።(እስከዛሬ)
፮ .ጌታ አምላክም ከሰማይ ወረደ።
፯.ስለፍቅርም ጉዳይ ተሰቀለ።
፰.ከሰውም ጥቂቱ አመነ።
፱.ያመነም ሁሉ አምላኩን ኢየሱስን አፈቀረ።
፲.ያፈቀረም ሁሉ ዳነ።
፲፩.እነሆም ሰው ዳግም ለመለኮት ፍቅር ተፈጠረ።
፲፪. ሰውም በፍቅር አረፈ፤ፈጣሪም በፍቅር ተከበረ።

No comments :

Post a Comment

Comment.Share.ይሳተፉ እንጂ።