ሕዝቡ የሚታየውን ብቻ በማየት- በሚታየው ብቻ ለመታየት እና የሚታየውንም ብቻ ለማሳየት ቁልቁል ከእንጦጦ ወደ ፒያሳ በአራት ኪሎ በኩል በኢተርኔት ጎዳና በፍጥነት ሲያዘግም - አንዳንድ ልጆች እና ህጻናቶች ብቻ ተራራው ላይ ብንጫወት ይሽለናል ደሞ ዙሪያገባው ሁሉ ይታየናል ብለው ዳገቱን ሲድሁ ታይተዋል።
Pages
»
እንደተቀበልኩት ምህረት እንደቸርነትህ ብዛት እንዳገለግልህ እርዳኝ ጌታ ሆይ ስጠኝ የመንፈስን እሳት"-በዚህ ዌብሎግ እውነተኛው የጌታ ኢየሱስ ባሪያ ተስፋዬ ጋቢሶ ይታወስ ዘንድ ወሰንን።This weblog has been dedicated to Tesfaye Gabiso,the faithful servant of The Lord.
Thursday, 24 February 2011
Sunday, 20 February 2011
የገንዘብ እንቅስቃሴ
ለ-ገንዘብ ወይም በ-ገንዘብ አልተንቀሳቀስንም -ወዳጆች ሆይ።ካሁን ኋላም ቢሆን ለ-ገንዘብ ወይም በ-ገንዘብ እንዳንንቀሳቀስ በክቡር የሰማይ አምላክ ፊት እንማጸናለን።
(ለ-ፍቅር በ-ፍቅር እንጂ።)
የረሳነውን አስታወስን፡-
ለዝና ወይም ለጭቃም አልተንቀሳቀስንም።
(ለ-ፍቅር በ-ፍቅር እንጂ።)
የረሳነውን አስታወስን፡-
ለዝና ወይም ለጭቃም አልተንቀሳቀስንም።
Labels:
የብላቴናው ጥቅሶች
Saturday, 19 February 2011
እንደማላውቅ እንደማውቅ ሁሉ እንደማውቅ ደሞ እንደማላውቅ ገና ወደፊት ይጠብቀኛል እንጂ።
ከእይምሮ የሚያልፍ ነገር እንደተደረገልኝ እንጂ የተደረገልኝን አሁን እንደማላውቅ እንደማውቅ ሁሉ -እንዲሁ ደሞ ወደሚቀጥለው ከተማ ስወሰድ የተደረገልኝን ሁሉ እንደማውቅ አውቃለሁ።
(ስለዚህ እላለሁ -ስለዚህ ገና አሁን በዚህ ከተማ ሳለሁ ይህቺን ነፍሴን አውልቄያት ከዚህ ወደዚያ ከተማ የምስጋና-አምልኮ ማሸጋገሪያ አደርጋታለሁ -በዚያም ከተማ ስደርስ አስቀድሜ ያሸሸሁት ሀብት ንብረቴ ወልዶ ከብዶ ተጠብቆ ይጠብቀኛል።ለዚህም ሽግግር ወደ ክርስቶስ ኢየሱስ የከተማዎች አስተዳዳሪ ማመልከቻየን በአደራ ደብዳቤ ሰድጀ -በማምለክም የሆነ ማመልከትህ ደርሶናል የሚል የመንፈስ የመልስ ደብዳቤ ደርሶኛል።እንኳን የክርስቶስ ከተማ የነአያሌው ከተማ አስተዳደር እንኳን "ደርሶናል" ይላልና።)
(ስለዚህ እላለሁ -ስለዚህ ገና አሁን በዚህ ከተማ ሳለሁ ይህቺን ነፍሴን አውልቄያት ከዚህ ወደዚያ ከተማ የምስጋና-አምልኮ ማሸጋገሪያ አደርጋታለሁ -በዚያም ከተማ ስደርስ አስቀድሜ ያሸሸሁት ሀብት ንብረቴ ወልዶ ከብዶ ተጠብቆ ይጠብቀኛል።ለዚህም ሽግግር ወደ ክርስቶስ ኢየሱስ የከተማዎች አስተዳዳሪ ማመልከቻየን በአደራ ደብዳቤ ሰድጀ -በማምለክም የሆነ ማመልከትህ ደርሶናል የሚል የመንፈስ የመልስ ደብዳቤ ደርሶኛል።እንኳን የክርስቶስ ከተማ የነአያሌው ከተማ አስተዳደር እንኳን "ደርሶናል" ይላልና።)
Labels:
የብላቴናው ጥቅሶች
Sunday, 6 February 2011
ምጥን የፍቅር ሕይወት ታሪክ
፩.ሰውም ከእግዚአብሔር ጋር በፍቅር ይኖር ዘንድ ተፈጠረ።
፪.ሰውም ተደናበረ።
፫. አዛምዶ ይቀኘው ተብሎም ፍቅር በምሳሌ ሔዋን በብርሌ ተጨመረ።
፬.ሰውም ይልቁን ሰክሮ ተደናበረ።
፭ .ሰውም በምሳሌ ተሰናከለ።(እስከዛሬ)
፮ .ጌታ አምላክም ከሰማይ ወረደ።
፯.ስለፍቅርም ጉዳይ ተሰቀለ።
፰.ከሰውም ጥቂቱ አመነ።
፱.ያመነም ሁሉ አምላኩን ኢየሱስን አፈቀረ።
፲.ያፈቀረም ሁሉ ዳነ።
፲፩.እነሆም ሰው ዳግም ለመለኮት ፍቅር ተፈጠረ።
፲፪. ሰውም በፍቅር አረፈ፤ፈጣሪም በፍቅር ተከበረ።
፪.ሰውም ተደናበረ።
፫. አዛምዶ ይቀኘው ተብሎም ፍቅር በምሳሌ ሔዋን በብርሌ ተጨመረ።
፬.ሰውም ይልቁን ሰክሮ ተደናበረ።
፭ .ሰውም በምሳሌ ተሰናከለ።(እስከዛሬ)
፮ .ጌታ አምላክም ከሰማይ ወረደ።
፯.ስለፍቅርም ጉዳይ ተሰቀለ።
፰.ከሰውም ጥቂቱ አመነ።
፱.ያመነም ሁሉ አምላኩን ኢየሱስን አፈቀረ።
፲.ያፈቀረም ሁሉ ዳነ።
፲፩.እነሆም ሰው ዳግም ለመለኮት ፍቅር ተፈጠረ።
፲፪. ሰውም በፍቅር አረፈ፤ፈጣሪም በፍቅር ተከበረ።
Labels:
የብላቴናው ጥቅሶች
Wednesday, 2 February 2011
ጭኮ በወይንጠጅ ብርሌ
አቤ ታየ። ከተኩል ዘመን በኋላ በኒውዮርክ ከተማ ወደ ሻሸመኔ በለንደን የእረኞች ቁጥቋጦ ጎዳና አቋርጦ ባዲሳባ በኩል ወደአዋሳ ባህር ዳር በናዝሬት ከተማ በጋሪ ሲጓዝ ሳለ - ወሬ ወዳጅ የጥንት የጠዋት የበሶዓለም ወዳጆቹ ካርቱም ላይ አግኝተውት - አቤ በሶ በቃኝ ብለህ ወደቤተክርስቶስ ያለም የሰማይ ንጉስ ግቢ ራስህን ወርውረህ አልነበር እንዴ ...እንዴት እንዲ ጸዳልህ ሁሉ የሚያበራዉ ምን ሆነህ ተገኘህ ሲሉ ጠይቀውት - ተሸወድን ወዳጆቼ ራሳችንን ሸወድን -በበሶ ተሸውደን ኖረናልና በበሶ እድሜያችን- ባልታወቀው በር መላእክት ቤተክርስቶስ ውስጥ በስውር ጭኮ በወይን ጠጅ ብርሌ ያቀርቡልኝ ነበርና።
Labels:
የብላቴናው ጥቅሶች
Tuesday, 1 February 2011
Subscribe to:
Posts
(
Atom
)