»

እንደተቀበልኩት ምህረት እንደቸርነትህ ብዛት እንዳገለግልህ እርዳኝ ጌታ ሆይ ስጠኝ የመንፈስን እሳት"-በዚህ ዌብሎግ እውነተኛው የጌታ ኢየሱስ ባሪያ ተስፋዬ ጋቢሶ ይታወስ ዘንድ ወሰንን።This weblog has been dedicated to Tesfaye Gabiso,the faithful servant of The Lord.

Tuesday, 31 December 2013

እጅግ የሚምር የሚራራ...

 አምላክ ነውና የኔ ጌታ ይድረሰው ምስጋና የኔ ጌታ ይድረሰው ምስጋና
...የሚል የጥንት ዘመን መዝሙር ትዝ አለኝ።እባክዎ ይበሉ ይቀጥሉ እርስዎ ይዘምሩ እንጂ 

Sunday, 29 December 2013

How Great Thou Art O LORD my GOD

Hewane Luv & Life Gardens » Song of the Week »How Great Thou Art O LORD my GOD.


A different version/with lyrics.

Thursday, 26 December 2013

ይህ የመለኮት ልጆች የሚዲያ ጣቢያ ነው





ለመንግስት ስራ ፈቃደኛ በመሆን አገልግሎት ላበረከተችው ለእህተ ተስፋ በጌታ (ከሬማ ማንቸስተር ቸርች) እናመሰግናለን።

መንግስት ያክብርሽ ይባርክሽ።

ስፔስ እና በጎነት ባንድ ላይ ላባረከቱ ለሬማ ማንቼ ወንድሞች፣ እህቶች እና መሪዎች እናመሰግናለን።

ከዚህ ቀደምም መንግስትን ለማገልገል በየበኩላቸው አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሁሉ እናመሰግናለን።

 ***
የመለኮት ልጆች የሚዲያ ጣቢያ ፕሮግራም ከዚህ ቀደም የት ተላልፏል?


  • ከሃያ መልካም አመታት በፊት በአዋሳ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን በ ዲ ኳየር ዓመታዊ በኣላት ላይ (በተለያየ መልኩ
  • ከጥቂት ዓመታት በፊት በሬማ ማንቸስተር ሚኒስትሪይ በዩናይትድ ኪንግደም። 
  • በቅርብ ዘመን በለንደን  በኪንግስ ክሮስ ዲስትሪክት በምትገኘው በኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተክርስቲያን በዩናይትድ ኪንግደም። 
  • በአሁን ዘመን በኢንተርኔት ከተማ በምትገኘው ማህበረ ምእመናን ። 
  • በዲጂታል ዘመን በጸጋFM ፣በYouTube ...በFB ገጾች ...ወዘተ። 
*** 
ለክብሩ ምስጋና። ክብር ለዘለዓለም ክብር ለስሙ። 

___________________________________ *** *** ***
እኛም በክርስቶስ ፍጹም የሚሆን ሰውን ሁሉ እናቀርብ ዘንድ ሰውን ሁሉ እየገሠጽን ሰውንም ሁሉ በጥበብ ሁሉ እያስተማርን የምንሰብከው እርሱ ነው። -ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1:28  ___________________________________
*** *** ***

Monday, 23 December 2013

ተመስገን ጌታ ሆይ።

ወደ እረፍት ማረፊያዎች በሰላም ስላደረስከን።
መሪያችን አንተው ነህ ሕያው አዛዣችን።

Sunday, 22 December 2013

There is no place I can hide from Your Love I can only survive through Your Love

Hewane Luv & Life Gardens » Song of the Week »

Your Love psalm 139, Oslo Gospel Choir


(በአቶ ኤዲተሩ በድጋሚ የተመረጠ - በፍቅር ብላጫ።)

Monday, 16 December 2013

ወደ አንተ አስገስግሰኝ

ጌታ ሆይ ሕይወቴን ተረከብ በአዲሱም ዘመን በፈቃድህ የክብር መንገድ ምራኝ እስከለዘላለሙ።
አሜን።

Sunday, 15 December 2013

ሕይወቴን ሙላልኝ በመስቀልህ ፍቅር

Hewane Luv & Life Gardens » Song of the Week » እንደተቀበልኩት ምህረት እንደቸርነትህ ብዛት

እንደተቀበልኩት
ምህረት
እንደቸርነትህ
ብዛት
እንዳገለግልህ
እርዳኝ
ጌታ
ሆይ
ስጠኝ
የመንፈስን
እሳት።

እስራቴን
ቆርጠህ
ቀንበሬን
ሰብረሃል
ነፍሴ
እንድታከብርህ
ነጻ
አውጥተኸኛል።

ባርነት
አበቃ
ልጅ
ነህ
ብለኸኛል
በደምህ
ቃልኪዳን
ያንተ
አድርገኸኛል።

*

የተፍገመገመ
ከውድቀት
እንዲተርፍ
የደከመን
ሁሉ
በቃል
እንድደግፍ
አንቃኝ
በማለዳ
ቀስቅሰኝ
ከእንቅልፍ
ታማኝ
ሎሌ
አድርገኝ
ልብን
የሚያሳርፍ።

*

ስንፍናዬን
አርቅ
በተግሳጽህ
በትር
እንድተጋም
እርዳኝ
ከጸጋህ
ዙፋን
ስር
ኢየሱስ
ያድናል
ብዬ
እንድመሰክር
ሕይወቴን
ሙላልኝ
በመስቀልህ
ፍቅር።

*

ጥበብ
ለሌላቸው
ለማያስተውሉ
ለተማሩም
ሰዎች
አውቀናል
ለሚሉ
ወንጌሉን
ልናገር
እንዲድኑ
አምነው
ለእነዚህ
ሁሉ
እዳዬ
ትልቅ
ነው።

*

ወንጌል
አይወሰን
አይቆጠብ
በክልል
እስከምድር
ዳር
ይሂድ
ቃልህ
ሳይከለከል
ለቅርቡም
ለሩቁም
ጽድቅህም
ይታደል
የሱስን
አግኝቶ
ፍጥረት
እሰይ
ይበል።

___

አሜን።

___
Click here to listen to the song from Wongelnet site.Album: Tesfaye Gabisso Abetu Mebarekin Barken Song no.13.

You have no idea ,how I love and respect Tesfaye Gabiso. I grew up under his feet -meaning- listening to his songs. He doesn't even know that I exist:- )I always had wished to be like him when I was a kid in my mother’s and father’s house ,almost three decades ago now, O’Lord, have you seen how time flies?

And this song "endetekebelikut mihiret" was my fav and is now and will be...."...esiraten koriteh keniberen sebirehal....nefise eniditakebireh ...nesta awutitehegnal....bedemih kal kidan yanite adirigehegnal..."

Pastor Gabiso is not only a singer-song writer, but also 'bale-kine'-a poet.

I solemnly suggest to those who closely know Tesfaye to create wikipedia and FB pages. If someone writes his biography, it will be a treasure.

With love and the joy of the Lord, I have indeed dedicated the entire hewane poetry page for his remarkable spiritual contributions to faith in Jesus Christ in Ethiopia.
Blessed be the Name of the Lord.
Amen.

Friday, 13 December 2013

የደግነትህ ብርታት

ጌታ ሆይ አመሰግናለሁ ስለረዳኸኝ ስራዬን ሁሉ ስለሰራኽልኝ።
ዕውቀትህ ማስተዋልህ ደግነትህ ሁሉ አይመረመርም። 

Sunday, 8 December 2013

አምላኬ ታማኝ ነው በመንገዱ

Hewane Luv & Life Gardens » Song of the Week »

ለገሠ ወተሮ
አምላኬ ታማኝ ነው በመንገዱ


አምላኬ ታማኝ ነው በመንገዱ (4)

በሐሩር ያሸዋ በረሃ ወይን አቆጠቆጠ
ጌታ በቃሉ ያለው ተፈፀመ
ቃሉ አይደክምምና በታላቁ ክንዱ ይሠራል
ለበረሃው ልብህ ፍሬ ይሰጣል
አዝ…

የሞተው ሁሉ ሲነሣ የማይሞት አካል ለብሶ
መበስበስ ላያይ ዳግም ተመልሶ
በዕድሜው ያፈራውን ሰው ሁሉ ያንኑ ያቀርባለ
ለጌታ የሚሆን ምን መከራ ይዘሃል
አዝ…

ከሥጋህ ነው ያጨድከው ወይስ ከርሱ ቅዱስ መንፈስ
ለሕይወት ይሆን ወይስ ለመበስበስ
መንገድህን አሁን ቀይር ፍሬህም አይቅር መና
የምሕረት ጊዜ አላለቀምና
አዝ…

ቢመስልህ ላንተ የተነፈገህ ደሞዝህ ዛሬ
ለድካምህ መኖ ለለቅሶህ ፍሬ
ታገል አትፍራ በርታ ጌታ አምላክህ ይረዳሃል
ለድካምህ አንድ ቀን አክሊል ይሰጣል
አዝ…

____
If you know where to find the video/audio,please advise.
Hewane Poetry Song of the Week Department.
With thanks.

ጌታ ትልቅ ታላቅም ነው።


Saturday, 7 December 2013

በአንድ ወፍ ሁለት ድንጋይ ላይ ሳርፍ።

ከአፈር ከጭቃ አንስተኸኝ በሁለት እግሮቼ ያቆምከኝ

  • ልምምድ ፩፪

በጌታ ፍቅር የሚወዱኝ ዘመድዎ  ድንገት ሳላስበው ውጥን ሳይኖረኝ  አፈር ከጭቃ አንስተኸኝ የተሰኘውን መዝሙር ከዘመርኩበት ካለፈው ሳምንት ዠምሮ ዛሬም እየዘመርኩ አለሁ ዘንድሮ


  • ልምምድ ፲



ኪይቦርድ የሚሉትን የሙዚቃ መሳሪያ እየተማርኩ ስላለሁ ለምን ከአፈር ከጭቃ የሚለው መዝሙር በኪቦርድ ሁናቴው ምን ሊመስል እንደሚችል  አላጤነውም ብዬ ልቤ ድንገት አስቤው ተነሳሳ

በመዠመሪያ ስዊንግ እና ጃዝ መስሎኝ ብዙ ለፋሁና አልሆን ሲለኝ ጊዜ ይህ ነገር ባላድ ይሆን እንዴ ብዬ ወደ ባላድ ሄድኩኝ።ባላድ አታለለኝ።ላካንስ የሚያታልል ነገር መዠሪያ ላይ የማያታልል ነው የሚመስለው

ልቤ ግን ነግሮኝ ነበር አልሰማም ብዬ ነው - እንደ ፈረስ ጉዞ ያለ ሶምሶማ ሊሆን እንደሚችል

አሁን ገና ደረስኩበት ብዬ ወደ ካንትሪ ሄድኩኝ።ካንትሪ በግልጽ ነው የነገረኝ - ሂድ ከዚህ ሂድልን ከዚህ በፊት ብዙ ተሳክቶልሃል ለዛሬ ግን አልተሳካልህም አምልጥ አለኝ አልተከራከርኩም

የሚራመድ ሰው ነው ላካስ ተጓዥ ሰው ሁለት ሶስቴ ወደፊት እየሮጠ (የሚሮጥ እየመሰለ)ወይስ በእውን እየሮጠ ነው አይታወቅም አየሮጠ የሚቆም የሚመስል ሰው

አለብን ሶምሶማ።
***
አርስዎ የምወድዎት ዘመዴ ታዲያ ክፋት የሌለው ጨዋታ ስለሚወዱ እነ ልምምድ ፩ ፣፪ ፣፫ ፣፬፣፮... ወዘተ የታሉ ብለው ፈታኝ ጥያቄ እንዳይጠይቁኝ ። የግድ የግድ መልስ ይሰጥ ከተባለ ግን እነርሱ እራሳቸው ለምን እየጠየቁም ብዬ  እንዴት ያለ ሰላማዊ ብስጭት እንዳበሳጩኝ ትዝ እያለኝ ሳያቸው ለካንስ ወደ ኢንተርኔትም ይሁን ወደ ዩቲዩቭ አንጓዝም ብለው አስፈቅደው ኖሯል

ጌታ ይመስገን።

ጌታ ሆይ ተመስገን።


Monday, 2 December 2013

ጌታ ፍጹም መልካም።


70ሺህ።

፸ሺህ ደረሰልን ።
(ሎተሪ እንዳይመስልዎት (ወይ ዕቁብ ))


አንድ ሚስጥር እንነግርዎታለን ከኛ ለእርስዎ።

ለቁጥር በቁጥር ስለ ቁጥር አልተንቀሳቀስንም

ዳሩ ግን ቁጥር በራሱ ጊዜ ቆጥሮ ፸ሺ ከደረሰ ዘንድ መቶ ሞልቶ ሊያስገርመን ምን ቀረው።

የሰራነውን ስራ ሰዎች  አይተው ተቀብለው ሲጠቀሙበት የጌታም ስም ሲከብርበት ማየት እጅጉን ደስ ያሰኛል ለማለት ነው።

መንፈሳዊ አገልግሎት ወይም ኑሮ ከምድራዊው (ዓለማዊ ) ያኗኗር ዘይቤ እጅጉን ይለያል ለምሳሌ በእንቅስቃሴዎት ሰውን አይተው በሰው ታይተው ለሰው ታይተው ሳይሆን ጌታን አይተው ለጌታ ታይተው ነው።

70,000 የደረሰው የዌብሎጋችን ጎብኚዎች ቁጥር ነው እንጂ።

ጌታ ይመስገን ክብር ለዘላለም ክብር ለስሙ ይሁን።

አስተያየት ለመስጠት guest book ላይ ክቡር ፊርማዎትን ለማኖር ወዘተ እባክዎ በዚች በኩል እልፍ ይበሉ።

Sunday, 1 December 2013